አምላኬ ሆይ! ልብን እንደምትመረምር፥ ቅንነትንም እንደምትወድድ አውቃለሁ፤ እኔም በልቤ ቅንነትና በፈቃዴ ይህን ሁሉ አቅርቤአለሁ፤ አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በፈቃዱና ደስ ተሰኝቶ እንዳቀረበልህ አይቻለሁ።
2 ዜና መዋዕል 35:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መሳፍንቱም ለሕዝቡና ለካህናቱ ለሌዋውያኑም በፈቃዳቸው ሰጡ፤ የጌታም ቤት አለቆች፥ ኬልቂያስ፥ ዘካርያስ፥ ይሒኤል፥ ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን ሁለት ሺህ ስድስት መቶ በጎችና ፍየሎች፥ ሦስት መቶም በሬዎች ለካህናቱ ሰጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሹማምቱም ለሕዝቡ፣ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ በገዛ ፈቃዳቸው አዋጥተው ሰጡ። የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አለቆች የሆኑት ኬልቅያስ፣ ዘካርያስና ይሒኤልም ለፋሲካ መሥዋዕት የሚቀርቡ ሁለት ሺሕ ስድስት መቶ በግ እንዲሁም ሦስት መቶ ወይፈን ሰጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የንጉሡ ባለሟሎች የሆኑ ባለሥልጣኖችም መሥዋዕት ሆነው የሚቀርቡ እንስሶችን በገዛ ፈቃዳቸው ለምእመናን፥ ለካህናትና ለሌዋውያን ሰጡ፤ የቤተ መቅደሱ አለቆች የሆኑት ሊቃነ ካህናቱ ሒልቂያ፥ ዘካርያስና ይሒኤልም የፋሲካ መሥዋዕት ሆነው የሚቀርቡ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ የበግና የፍየል ጠቦቶችንና ሦስት መቶ በሬዎችን ለካህናት ሰጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቆቹም ለሕዝቡና ለካህናቱ፥ ለሌዋውያኑም በፈቃዳቸው ሰጡ፤ የእግዚአብሔርም ቤት አለቆች፥ ኬልቅያስ፥ ዘካርያስ፥ ኢዮሔል፥ ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን ሁለት ሺህ ስድስት መቶ በጎችንና ፍየሎችን፥ ሦስት መቶም በሬዎችን ለካህናቱ ሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መሳፍንቱም ለሕዝቡና ለካህናቱ ለሌዋውያኑም በፈቃዳቸው ሰጡ፤ የእግዚአብሔርም ቤት አለቆች፥ ኬልቂያስ፥ ዘካርያስ፥ ይሒኤል፥ ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን ሁለት ሺህ ስድስት መቶ በጎችና ፍየሎች፥ ሦስት መቶም በሬዎች ለካህናቱ ሰጡ። |
አምላኬ ሆይ! ልብን እንደምትመረምር፥ ቅንነትንም እንደምትወድድ አውቃለሁ፤ እኔም በልቤ ቅንነትና በፈቃዴ ይህን ሁሉ አቅርቤአለሁ፤ አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በፈቃዱና ደስ ተሰኝቶ እንዳቀረበልህ አይቻለሁ።
እንዲህም ያከበሩት የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ እንደ ቁርባን ስለሚቀርበው መሥዋዕት አንድ ሺህ ወይፈኖችና ሰባት ሺህ በጎች እንዲሁም ሹማምንቱ አንድ ሺህ ወይፈኖችና ዐሥር ሺህ በጎች ለጉባኤው ሰጥተው ስለ ነበረ ነው።
በንጉሡም በሕዝቅያስና በጌታ ቤት አለቃ በዓዛርያስ ትእዛዝ ይሒዒል፥ ዓዛዝያ፥ ናሖት፥ አሣሄል፥ ይሬሞት፥ ዮዛባት፥ ኤሊኤል፥ ሰማኪያ፥ መሐት፥ በናያስ፥ ከኮናንያና ከወንድሙ ከሰሜኢ እጅ በታች ተቈጣጣሪዎች ነበሩ።
ወደ ታላቁም ካህን ወደ ኬልቅያስ መጡ፤ ሌዋውያኑም የደጆቹም ጠባቂዎች ከምናሴና ከኤፍሬም ከቀረውም ከእስራኤል ሁሉ፥ ከይሁዳና ከብንያም ሁሉ በኢየሩሳሌምም ከሚኖሩት የሰበሰቡትን፥ ወደ ጌታ ቤት ያመጡትን ገንዘብ ሰጡት።
ኢዮስያስም ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን በዚያ ለነበሩት ለሕዝቡ ልጆች ከመንጋው ሠላሳ ሺህ የበግና የፍየል ጠቦቶች፥ ሦስት ሺህም በሬዎች ሰጣቸው፤ እነዚህም ከንጉሡ ሀብት ነበሩ።
በዙሪያቸውም ያሉ ሁሉ በፈቃዳቸው ካቀረቡት መባ ሁሉ በተጨማሪ በእጃቸው፥ በብር ዕቃና በወርቅ፥ በዕቃዎችና በእንስሶችና በውድ ነገሮች አበረታቱአቸው።
በባቢሎንም አውራጃ ሁሉ የምታገኘውን ብርና ወርቅ በሙሉ፥ ሕዝቡና ካህናቱም በኢየሩሳሌም ላለው ለአምላካቸው ቤት በፈቃዳቸው የሚሰጡትን ይዘህ ሂድ።