2 ዜና መዋዕል 33:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምናሴም ጌታ ከእስራኤል ልጆች ፊት ካጠፋቸው ከአሕዛብ ይልቅ ክፉ እንዲሠሩ በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምናሴ ግን እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ፊት ካጠፋቸው አሕዛብ የባሰ ክፉ ድርጊት ይፈጽሙ ዘንድ፣ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ አሳተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምናሴ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ፥ የእስራኤል ልጆች ወደ ተስፋይቱ አገር በሚገቡበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከፊታቸው እንዲባረሩ ያደረጋቸው ሕዝቦች ካደረጉት ይበልጥ የከፋ ኃጢአት እንዲሠሩ አደረጋቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምናሴም እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት ካጠፋቸው ከአሕዛብ ይልቅ ክፉ ይሠሩ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምናሴም እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት ካጠፋቸው ከአሕዛብ ይልቅ ክፉ ይሠሩ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳተ። |
ምናሴ የይሁዳን ሕዝብ ወደ ጣዖት አምልኮና እግዚአብሔርን ወደሚያሳዝን ኃጢአት ከመምራት አልፎ፥ ንጹሓን የሆኑትን ብዙ ሰዎችን በመፍጀት የኢየሩሳሌምን መንገዶች በደም እንዲጥለቀለቁ አድርጎአል።
ነገር ግን ይህም ሁሉ ሆኖ ንጉሥ ምናሴ ባደረገው ክፉ ነገር ምክንያት በይሁዳ ላይ የነደደው አስፈሪ የእግዚአብሔር ቁጣ እስከ አሁን ድረስ ገና አልበረደም ነበር።
እንዲሁም ጌታ ለዳዊትና ለልጁ ለሰለሞን፦ “እኔ ያዘዝኋቸውን ሁሉ፥ በሙሴም በኩል የተሰጠውን ሕግና ሥርዓት ፍርድንም ሁሉ ቢያደርጉ ቢጠብቁም፥ ለአባቶቻችሁ ከሰጠኋት ምድር እስራኤል እንደገና እንዲሰደዱ አላደርግም” ብሎ ነበር።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሁካታችሁ በዙሪያችሁ ካሉት አገሮች ይልቅ ሆኗል፥ በትእዛዜም አልሄዳችሁምና፥ ፍርዴንም አልጠበቃችሁምና፥ በዙሪያችሁም እንዳሉ እንደ አሕዛብ ፍርድ እንኳ አላደረጋችሁምና
የዖምሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቀሃልና፥ በምክራቸውም ሄዳችኋልና፤ ስለዚህ አንተን ለጥፋት ነዋሪዎቿን ደግሞ ለመዘባበቻ ሰጥቻችኋለሁ፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።
እኔም በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ተቀመጡበት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ፤ ከእናንተም ጋር ተዋጉ፥ አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋችሁ፥ ምድራቸውንም ወረሳችሁ፤ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው።