2 ዜና መዋዕል 33:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአገሩ ሕዝብ ግን በንጉሡ በአሞጽ ላይ ያሤሩበትን ሁሉ ገደሉ፤ የአገሩም ሕዝብ ልጁን ኢዮስያስን በእርሱ ፋንታ አነገሡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የአገሩ ሕዝብ በንጉሥ አሞን ላይ ያሤሩትን ሁሉ ገደሉ፤ ልጁን ኢዮስያስንም በምትኩ አነገሡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳም ሕዝብ የአሞንን ገዳዮች ገድለው በእርሱ እግር ልጁን ኢዮስያስን አነገሡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዘለዓለም ክፋቴን አትመልከትብኝ፤ በምድር ጥልቀትም አትበቀለኝ፤ አቤቱ፥ በንስሓ ለሚመለሱ ሰዎች፥ አምላካቸው አንተ ነህና፥ ቸርነትህ በእኔ ላይ ይገለጥ፤ መዳን የማይገባኝ ሲሆን በይቅርታህ ብዛት አዳንኸኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአገሩ ሕዝብ ግን በንጉሡ በአሞን ላይ የተማማሉትን ሁሉ ገደሉ፤ የአገሩም ሕዝብ ልጁን ኢዮስያስን በእርሱ ፋንታ አነገሡ። |