የጌታ መልአክ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፥ ጌታ ስለ ክፉው ነገር አዘነ፤ ሕዝቡን የሚቀሥፈውንም መልአክ “ይበቃል! እጅህን መልስ” አለው። በዚያን ጊዜ የጌታ መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
2 ዜና መዋዕል 32:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ጽኑዓን ኃያላኑንና መሳፍንቱን የጦር አዛዦቹንም ከአሦር ንጉሥ ሰፈር እንዲያጠፋ መልአኩን ላከ። የአሦርም ንጉሥ አፍሮ ወደ አገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩም ቤት በገባ ጊዜ ከአብራኩ የወጡት ልጆቹ በዚያ በሰይፍ ገደሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም መልአክ ልኮ በአሦር ንጉሥ ሰፈር ተዋጊዎችን፣ መሪዎችንና የጦር መኰንኖችን እንዲያጠፋቸው አደረገ። ስለዚህ ንጉሡ በውርደት ወደ ገዛ አገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩ ቤተ ጣዖት እንደ ገባም፣ የገዛ ልጆቹ በሰይፍ ገደሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም መልአክን ልኮ የአሦርን ወታደሮችና የጦር መኰንኖች እንዲገደሉ አደረገ፤ ስለዚህም የአሦር ንጉሠ ነገሥት ተዋርዶ ወደ አገሩ ተመለሰ፤ አንድ ቀን በአምላኩ መስገጃ ስፍራ በነበረበት ወቅት የገዛ ልጆቹ በሰይፍ ገደሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም መልአኩን ላከ፤ እርሱም ጽኑዓን ኀያላኑንና መሳፍንቱን አለቆቹንም ከአሦር ንጉሥ ሰፈር አጠፋ። የአሦርም ንጉሥ አፍሮ ወደ ሀገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩም ቤት በገባ ጊዜ ከወገቡ የወጡት ልጆቹ በዚያ በሰይፍ ገደሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ጽኑዓን ኃያላኑንና መሳፍንቱን አለቆቹንም ከአሦር ንጉሥ ሰፈር እንዲያጠፋ መልአኩን ሰደደ። የአሦርም ንጉሥ አፍሮ ወደ አገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩም ቤት በገባ ጊዜ ከወገቡ የወጡት ልጆቹ በዚያ በሰይፍ ገደሉት። |
የጌታ መልአክ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፥ ጌታ ስለ ክፉው ነገር አዘነ፤ ሕዝቡን የሚቀሥፈውንም መልአክ “ይበቃል! እጅህን መልስ” አለው። በዚያን ጊዜ የጌታ መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
ከዚህ በኋላ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፦ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ስለ አሦር ንጉሠ ነገሥት ስለ ሰናክሬም ዛቻ ያቀረብከውን ጸሎት ሰምቻለሁ፤
እንዲሁም ጌታ ሕዝቅያስንና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ከአሦር ንጉሥ ከሰናክሬም እጅ ከጠላቶቻቸውም ሁሉ እጅ አዳናቸው፤ በዙሪያቸውም ካለው ሁሉ አሳረፋቸው።
የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ ወደ ሕዝቅያስ ላከ፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰናክሬም ወደ እኔ ለምነሀልና
“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይወጋናልና ስለ እኛ፥ እባክህ፥ ጌታን ጠይቅ፤ ምናልባትም ጌታ ለእኛ እንደ ተአምራቱ ሁሉ አድርጐ ከእኛ እንዲመለስ ያደርገዋልና።”