2 ዜና መዋዕል 32:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተማይቱንም ወርሮ ለመውሰድ፥ በቅጥርም ላይ የተቀመጡትን የኢየሩሳሌም ሕዝብ ለማስፈራራትና ለማስደንገጥ፥ በታላቅ ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ይጮኹባቸው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በማስደንገጥና በማስፈራራት ከተማዪቱን ለመያዝ ሲሉ በቅጥሩ ላይ ወደ ተቀመጠው ወደ ኢየሩሳሌም ሕዝብ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በዕብራይስጥ ጮኹ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአሦር ባለሥልጣኖች ይህን የዛቻ ቃል በዕብራይስጥ ቋንቋ በቅጽሮቹ ላይ ለነበሩት ለኢየሩሳሌም ሰዎች ከፍ ባለ ድምፅ ያሰሙ ነበር፤ ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት ሕዝቡን አስፈራርተው ተስፋ በማስቈረጥ ከተማይቱን በቀላል ለመያዝ ዐቅደው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቅጥሩን እንዲያፈርሱ ከተማዪቱንም እንዲወስዱ፥ በቅጥር ላይ የተቀመጡትን የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ያስፈራቸውና ያስደነግጣቸው ዘንድ በታላቅ ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ይጮኽባቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተማይቱንም እንዲወስዱ፥ በቅጥር ላይ የተቀመጡትን የኢየሩሳሌም ሕዝብ ያስፈሩና ያስደነግጡ ዘንድ፥ በታላቅ ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ይጮኹባቸው ነበር። |
ዳዊት በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች፥ “ይህን ፍልስጥኤማዊ ገድሎ እንዲህ ያለውን ውርደት ከእስራኤል ለሚያስወግድ ሰው ምን ይደረግለታል? ደግሞስ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ይገዳደር ዘንድ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ እርሱ ማነው?” ሲል ጠየቀ።