2 ዜና መዋዕል 3:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓምዶቹንም አንደኛውን በቀኝ፥ ሁለተኛውን በግራ በመቅደሱ ፊት አቆማቸው፥ በቀኝም የነበረውን ስም ያኪን በግራም የነበረውን ስም ቦዔዝ ብሎ ጠራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐምዶቹንም አንዱን በደቡብ፣ ሌላውን በሰሜን አድርጎ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በስተ ደቡብ ያቆመውን ዐምድ፣ “ያኪን”፣ በስተሰሜን ያለውንም፣ “ቦዔዝ” ብሎ ጠራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምሰሶዎቹም የቆሙት በቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ግራና ቀኝ ነበር፤ በደቡብ በኩል የቆመው ምሰሶ “ያኪን” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፥ በሰሜን በኩል የቆመው ደግሞ “ቦዔዝ” ተብሎ ይጠራ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዕማዶቹንም አንደኛውን በቀኝ፥ ሁለተኛውንም በግራ በመቅደሱ ፊት አቆማቸው፤ በቀኝም የነበረውን ስም ርትዕ በግራም የነበረውን ስም ጽንዕ ብሎ ጠራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓምዶቹንም አንደኛውን በቀኝ፥ ሁለተኛውን በግራ በመቅደሱ ፊት አቆማቸው፤ በቀኝም የነበረውን ስም “ያቁም” በግራም የነበረውን ስም “በለዝ” ብሎ ጠራቸው። |
ሑራም ከነሐስ የተሠሩትን ሁለት ምሰሶዎች በቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ፊት ለፊት አቆማቸው፤ ከቤተ መቅደሱ መግቢያ በር በስተ ደቡብ በኩል የቆመው ምሰሶ “ያኪን” ተብሎ ተጠራ፤ በስተ ሰሜን በኩል የቆመው ምሰሶ ደግሞ ቦዔዝ ተባለ።
የመተላለፊያው ርዝመት ሀያ ክንድ፥ ወርዱ ደግሞ ዐሥራ አንድ ክንድ ነበረ፤ ወደ እርሱም የሚያደርሱ ደረጃዎች ነበሩ፤ አንድ በዚህ ወገን አንድ በዚያ ወገን ሆነው በመቃኖቹ አጠገብ የግንብ አዕማድ ነበሩ።