Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 3:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ምሰሶዎቹም የቆሙት በቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ግራና ቀኝ ነበር፤ በደቡብ በኩል የቆመው ምሰሶ “ያኪን” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፥ በሰሜን በኩል የቆመው ደግሞ “ቦዔዝ” ተብሎ ይጠራ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ዐምዶቹንም አንዱን በደቡብ፣ ሌላውን በሰሜን አድርጎ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በስተ ደቡብ ያቆመውን ዐምድ፣ “ያኪን”፣ በስተሰሜን ያለውንም፣ “ቦዔዝ” ብሎ ጠራቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ዓምዶቹንም አንደኛውን በቀኝ፥ ሁለተኛውን በግራ በመቅደሱ ፊት አቆማቸው፥ በቀኝም የነበረውን ስም ያኪን በግራም የነበረውን ስም ቦዔዝ ብሎ ጠራቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 አዕ​ማ​ዶ​ቹ​ንም አን​ደ​ኛ​ውን በቀኝ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም በግራ በመ​ቅ​ደሱ ፊት አቆ​ማ​ቸው፤ በቀ​ኝም የነ​በ​ረ​ውን ስም ርትዕ በግ​ራም የነ​በ​ረ​ውን ስም ጽንዕ ብሎ ጠራ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ዓምዶቹንም አንደኛውን በቀኝ፥ ሁለተኛውን በግራ በመቅደሱ ፊት አቆማቸው፤ በቀኝም የነበረውን ስም “ያቁም” በግራም የነበረውን ስም “በለዝ” ብሎ ጠራቸው።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 3:17
4 Referencias Cruzadas  

የስምዖን ልጆች፦ ይሙኤል፥ ያሚን፥ ኦሃድ፥ ያኪን፥ ጾሐርና ከከነዓናዊቷ ሴት የተወለደው ሻኡል ናቸው።


ሑራም ከነሐስ የተሠሩትን ሁለት ምሰሶዎች በቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ፊት ለፊት አቆማቸው፤ ከቤተ መቅደሱ መግቢያ በር በስተ ደቡብ በኩል የቆመው ምሰሶ “ያኪን” ተብሎ ተጠራ፤ በስተ ሰሜን በኩል የቆመው ምሰሶ ደግሞ ቦዔዝ ተባለ።


የምሰሶዎቹም ጫፎች የመርበብ ቅርጽ ባላቸው ሰንሰለቶችና ከነሐስ በተሠሩ ቊጥራቸው አንድ መቶ በሆነ የሮማን ፍሬ አምሳል የተሠራ ቅርጽ ተስሎባቸው ነበር፤


የመግቢያው ክፍል ርዝመት ኻያ ክንድ፥ ወርዱ ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበር፤ ዐሥር የመወጣጫ ደረጃዎቹም ወደዚያ ያደርሱ ነበር፤ በሁለቱ መወጣጫ ደረጃዎች ጐን ዐምዶች ነበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos