2 ዜና መዋዕል 29:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለመግፈፍ ጥቂቶች ነበሩ፤ ስለዚህም ሌዋውያን በቅን ልብ ከካህናት ይልቅ ይቀደሱ ነበርና ሥራው እስኪፈጸም ድረስ፥ ካህናቱም እስኪቀደሱ ድረስ ወንድሞቻቸው ሌዋውያን ያግዙአቸው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ቈዳ ሁሉ ለመግፈፍ ቍጥራቸው እጅግ ጥቂት ነበር፤ ስለዚህ ወገኖቻቸው የሆኑት ሌዋውያን ሥራው እስኪያልቅና ሌሎች ካህናት እስኪቀደሱ ድረስ ረዷቸው፤ ሌዋውያኑም ራሳቸውን ለመቀደስ ከካህናቱ ይልቅ ጠንቃቆች ነበሩና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ሁሉ እንስሳ ዐርደው ቆዳውን ለመግፈፍ በቂ ካህናት ስላልነበሩ ሥራው እስኪጠናቀቅና የነጹ ካህናት እስከሚገኙ ድረስ ሌዋውያን ይረዱአቸው ነበር፤ በመንጻት ረገድ ከካህናት ይልቅ ሌዋውያን ዘወትር ዝግጁዎች ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ካህናቱ ጥቂቶች ነበሩና የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለመግፈፍ አይችሉም ነበር፤ ስለዚህም ሌዋውያን በቅን ልብ ከካህናት ይልቅ ይቀደሱ ነበርና ሥራው እስኪፈጸም ድረስ፥ ካህናቱም እስኪቀደሱ ድረስ ወንድሞቻቸው ሌዋውያን ያግዙአቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለመግፈፍ ጥቂቶች ነበሩ፤ ስለዚህም ሌዋውያን በቅን ልብ ከካህናት ይልቅ ይቀደሱ ነበርና ሥራው እስኪፈጸም ድረስ፥ ካህናቱም እስኪቀደሱ ድረስ ወንድሞቻቸው ሌዋውያን ያግዙአቸው ነበር። |
አምላኬ ሆይ! ልብን እንደምትመረምር፥ ቅንነትንም እንደምትወድድ አውቃለሁ፤ እኔም በልቤ ቅንነትና በፈቃዴ ይህን ሁሉ አቅርቤአለሁ፤ አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በፈቃዱና ደስ ተሰኝቶ እንዳቀረበልህ አይቻለሁ።
እንዲህም አላቸው፦ “ሌዋውያን ሆይ! ስሙኝ፤ ተቀደሱ፥ የአባቶቻችሁንም አምላክ የጌታን ቤት ቀድሱ፤ ርኩሱንም ነገር ሁሉ ከመቅደሱ አስወግዱ።
በሁለተኛውም ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካውን ጠቦት አረዱ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አዋረዱ፥ ተቀደሱም፥ ወደ ጌታም ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ።
እንዲህም ያከበሩት የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ እንደ ቁርባን ስለሚቀርበው መሥዋዕት አንድ ሺህ ወይፈኖችና ሰባት ሺህ በጎች እንዲሁም ሹማምንቱ አንድ ሺህ ወይፈኖችና ዐሥር ሺህ በጎች ለጉባኤው ሰጥተው ስለ ነበረ ነው።
ዳሩ ግን በጊዜው ለማክበር አልቻሉም ነበር ምክንያቱም በቊጥር በቂ የሆኑ ካህናት ስላልተቀደሱ፥ ሕዝቡም ገና በኢየሩሳሌም ስላልተሰባሰቡ ነበር።
ካህናቱና ሌዋውያኑ እንደ አንድ ሰው ሆነው እራሳቸውን አነጹ፥ ሁሉም ንጹሐን ነበሩ፥ ከምርኮ ለተመለሱ ሕዝቦች ሁሉ፥ ለወንድሞቻቸው ለካህናቱና ለራሳቸው ፋሲካውን አረዱ።
በመቅደሴ ውስጥ አገልጋዮች፥ በቤቱም በሮች ዘበኞች ይሆናሉ፥ በቤቱም ውስጥ ያገለግላሉ፤ ለሕዝቡም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና መሥዋዕትን ያርዳሉ፥ ሊያገለግሉአቸውም በፊታቸው ይቆማሉ።
እነርሱም ትእዛዝህን የድንኳኑንም ሁሉ አገልግሎት ግዴታ ይፈጽሙ፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ፥ እናንተም ደግሞ ከእነርሱ ጋር እንዳትሞቱ፥ እነርሱ ወደ መቅደሱ ዕቃና ወደ መሠዊያው አይቅረቡ።
የእስራኤልም ልጆች ወደ መቅደሱ በቀረቡ ጊዜ መቅሠፍት እንዳያገኛቸው፥ ለእስራኤል ልጆች እንዲያስተስርዩላቸው፥ የእስራኤልንም ልጆች አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ እንዲሠሩ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለአሮንና ለልጆቹ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአቸዋለሁ።”