| 2 ዜና መዋዕል 29:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)35 እጅግ ብዙ ከነበረው የሚቃጠል መሥዋዕት ጋር የአንድነቱ መሥዋዕት ስብ ነበረ፤ ለሚቃጠለውም መሥዋዕት የሚቀርበው የመጠጥ ቁርባን በዚያ ነበረ። እንዲህ ባለ መንገድ የጌታ ቤት አገልግሎት ተዘጋጀ።Ver Capítulo አዲሱ መደበኛ ትርጒም35 ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋራ የሚቀርበውን የኅብረት መሥዋዕት ሥብና የመጠጡን ቍርባን ጨምሮ የሚቃጠለው መሥዋዕት እጅግ ብዙ ነበር። በዚህ ሁኔታም የእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት እንደ ገና ተደራጀ።Ver Capítulo አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም35 ብዙ ከሆነው የሚቃጠል መሥዋዕት ለደኅንነት መሥዋዕት የሚቀርበው ስብ ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር የሚቀርበው የመጠጥ ቊርባን ነበር። በዚህ ሁኔታ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚደረገው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት እንደገና ተጀመረ፤Ver Capítulo የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)35 የሚቃጠለውም መሥዋዕት ከደኅንነቱ መሥዋዕት ስብና ለሚቃጠለውም መሥዋዕት ከሚቀርበው የመጠጥ ቍርባን ጋር ብዙ ነበረ። እንዲሁም የእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ተዘጋጀ።Ver Capítulo መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)35 የሚቃጠለውም መሥዋዕት የደኅንነቱም መሥዋዕት ስብ፥ ከሚቃጠለውም መሥዋዕት ሁሉ ጋር የሚቀርበው የመጠጥ ቍርባን፥ ብዙ ነበረ። እንዲሁም የእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ተዘጋጀ።Ver Capítulo |