ስለዚህ ዳዊት የጌታን ታቦት አብሮት እንዲሆን ወደ ዳዊት ከተማ ይዞት ለመሄድ አልፈለገም፤ በዚህ ፈንታ አቅጣጫ ለውጦ የጌት ሰው ወደ ሆነው ወደ ዖቤድ ኤዶም ቤት ወሰደው።
2 ዜና መዋዕል 25:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወርቁንና ብሩን ሁሉ፥ በጌታም ቤት ከዖቤድኤዶም ጋር የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ፥ የንጉሡም ቤት መዛግብት፥ በመያዣ የተያዙትንም ወስዶ ወደ ሰማርያ ተመለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በአቢዳራ ጥበቃ ሥር የነበረውንና በአምላክ ቤተ መቅደስ የተገኘውን ወርቅ፣ ጥሬ ብርና ዕቃ በሙሉ፣ ከቤተ መንግሥቱም ንብረትና በመያዣ ከያዛቸው ሰዎች ጭምር ወስዶ ወደ ሰማርያ ተመለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤተ መቅደስ የነበረውን ወርቅና ብር ሁሉ፥ በዖቤድኤዶም ዘሮች ይጠበቁ የነበሩትን የቤተ መቅደሱን ዕቃዎችና የቤተ መንግሥቱን ሀብት በሙሉ ምርኮ አድርጎ በመያዣም ስም የወሰዳቸውን ሰዎች በመውሰድ ወደ ሰማርያ ይዞ ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወርቁንና ብሩን ሁሉ፥ በእግዚአብሔርም ቤት በአብዲዶም እጅ የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ፥ በንጉሡም ቤተ መዛግብት የተገኘውን፥ በመያዣ የተያዙትንም ልጆች ወስዶ ወደ ሰማርያ ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወርቁንና ብሩን ሁሉ፥ በእግዚአብሔርም ቤት ከዖቤድኤዶም ጋር የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ፥ የንጉሡም ቤት መዛግብት፥ በመያዣ የተያዙትንም ወስዶ ወደ ሰማርያ ተመለሰ። |
ስለዚህ ዳዊት የጌታን ታቦት አብሮት እንዲሆን ወደ ዳዊት ከተማ ይዞት ለመሄድ አልፈለገም፤ በዚህ ፈንታ አቅጣጫ ለውጦ የጌት ሰው ወደ ሆነው ወደ ዖቤድ ኤዶም ቤት ወሰደው።
በዚያም ያገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ፥ የቤተ መቅደሱን ንዋያተ ቅድሳትና የቤተ መንግሥቱን ሀብት ሁሉ ጭኖ ወደ ሰማርያ ተመለሰ፤ በመያዣ ስም የተማረኩ ሰዎችንም ይዞ ሄደ።
የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ የጌታንም ቤት መዛግብትና የንጉሡን ቤት መዛግብት ወሰደ፤ ሁሉንም ነገር ወሰደ፤ ደግሞም ሰሎሞን የሠራቸውን የወርቁን ጋሻዎች ወሰደ።