2 ዜና መዋዕል 25:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮአስ የይሁዳን ንጉሥ የአካዝያስን ልጅ የኢዮአስን ልጅ አሜስያስን በቤት-ሳሚስ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር ከኤፍሬም በር ጀምሮ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ አራት መቶ ክንድ አፈረሰ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 የእስራኤል ንጉሥ ዮአስም የአካዝያስን የልጅ ልጅ የኢዮአስን ልጅ የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስን ቤትሳሚስ ላይ ማርኮ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፤ ከኤፍሬም በር እስከ ማእዘኑ በር ድረስ አራት መቶ ክንድ ያህል ርዝመት ያለውን የኢየሩሳሌምን ቅጥር አፈረሰ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ንጉሥ ዮአስም አሜስያስን ማርኮ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደው፤ ከኤፍሬም ቅጽር በር አንሥቶ እስከ ማእዘን ቅጽር በር ድረስ ያለውን ርዝመቱ ሁለት መቶ ሜትር ያኽል የሆነውን የኢየሩሳሌምን ቅጽር አፈረሰ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮአስ የይሁዳን ንጉሥ የአካዝያስን ልጅ የኢዮአስን ልጅ አሜስያስን በቤትሳሚስ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር ከኤፍሬም በር ጀምሮ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ አራት መቶ ክንድ አፈረሰ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮአስ የይሁዳን ንጉሥ የአካዝያስን ልጅ የኢዮአስን ልጅ አሜስያስን በቤትሳሚስ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር ከኤፍሬም በር ጀምሮ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ አራት መቶ ክንድ አፈረሰ። Ver Capítulo |