ኢዩ መሥዋዕቱን አቅርቦ እንዳበቃ ወዲያውኑ ለዘብ ጠባቂዎችና ለጦር መኰንኖች “ገብታችሁ እነዚህን ሁሉ ግደሉ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” ሲል አዘዛቸው፤ እነርሱም ሰይፍ ሰይፋቸውን በመምዘዝ ገብተው ሁሉንም ገደሉ፤ ሬሳቸውንም ሁሉ እየጐተቱ ወደ ውጪ አወጡት፤ ከዚህም በኋላ ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ገብተው፥
2 ዜና መዋዕል 23:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም ዮዳሄ በጭፍራው ላይ የተሾሙትን የመቶ አለቆች፦ “ከሰልፉ መካከል አውጡአት የሚከተላትም በሰይፍ ይገደል” ብሎ አዘዛቸው። ካህኑም፦ “በጌታ ቤት ውስጥ አትግደሉአት” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑ ዮዳሄም የወታደሮች አዛዥ ወደሆኑት ወደ መቶ አለቆቹ፣ “በሰልፉ መካከል አውጥታችሁ አምጧት፤ የሚከተላት ካለም በሰይፍ ግደሉት” ሲል ላከባቸው። ካህኑም፣ “በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አትግደሏት” ብሎ ነበርና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮዳሄ በበኩሉ ዐታልያ በቤተ መቅደሱ ክልል ውስጥ እንድትገደል አልፈለገም፤ ስለዚህም የጦር መኰንኖቹን ጠርቶ “ግራና ቀኝ በተሰለፉት ዘቦች መካከል አውጥታችሁ ውሰዱአት፤ እርስዋን ከሞት ለማትረፍ የሚሞክር ሰው ቢኖር ግደሉት” ሲል አዘዛቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ኢዮአዳ ወጥቶ በጭፍራው ላይ የተሾሙትን አለቆችና የመቶ አለቆች፥ “ከቤተ እግዚአብሔር ወደ ውጭ አውጡአት፤ የሚከተላትም በሰይፍ ይገደል” ብሎ አዘዛቸው። ካህኑ፥ “በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ አትገደል” ብሎአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ዮዳሄ በጭፍራው ላይ የተሾሙትን የመቶ አለቆች “ወደ ሰልፉ መካከል አውጡአት የሚከተላትም በሰይፍ ይገደል” ብሎ አዘዛቸው። ካህኑም “በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ አትግደሉአት” አለ። |
ኢዩ መሥዋዕቱን አቅርቦ እንዳበቃ ወዲያውኑ ለዘብ ጠባቂዎችና ለጦር መኰንኖች “ገብታችሁ እነዚህን ሁሉ ግደሉ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” ሲል አዘዛቸው፤ እነርሱም ሰይፍ ሰይፋቸውን በመምዘዝ ገብተው ሁሉንም ገደሉ፤ ሬሳቸውንም ሁሉ እየጐተቱ ወደ ውጪ አወጡት፤ ከዚህም በኋላ ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ገብተው፥
ዮዳሄ በበኩሉ ዐታልያ በቤተ መቅደሱ ክልል ውስጥ እንድትገደል አልፈለገም፤ ስለዚህም የጦር አለቆቹን “ግራና ቀኝ በተሰለፉት ዘቦች መካከል አውጥታችሁ ውሰዱአት፤ እርሷን ለመከተል የሚሞክር ቢኖር ይገደል” ሲል አዘዛቸው።
ንጉሥ ኢዮአስን በዙሪያው በምትጠብቁበትም ጊዜ ሰይፋችሁን መዛችሁ ወደሚሄድበት ስፍራ ሁሉ አብራችሁ ሂዱ፤ ወደ እናንተ ለመቅረብ የሚደፍር ማንም ቢኖር ይገደል።”
እነሆም፥ ንጉሡ በመግቢያው በዓምዱ አጠገብ ሆኖ ከንጉሡም ጋር አለቆችና መለከተኞች ቆመው አየች። የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ ብሎአቸው መለከቱን ይነፉ ነበር፤ መዘምራንም በዜማ ዕቃ እያዜሙ የምስጋና መዝሙር ይዘምሩ ነበር። ጎቶሊያም ልብስዋን ቀድዳ፦ “ዓመጽ ነው፥ ዓመጽ ነው” ብላ ጮኸች።