Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 23:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ካህ​ኑም ኢዮ​አዳ ወጥቶ በጭ​ፍ​ራው ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን አለ​ቆ​ችና የመቶ አለ​ቆች፥ “ከቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ውጭ አው​ጡ​አት፤ የሚ​ከ​ተ​ላ​ትም በሰ​ይፍ ይገ​ደል” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው። ካህኑ፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ አት​ገ​ደል” ብሎ​አ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ካህኑ ዮዳሄም የወታደሮች አዛዥ ወደሆኑት ወደ መቶ አለቆቹ፣ “በሰልፉ መካከል አውጥታችሁ አምጧት፤ የሚከተላት ካለም በሰይፍ ግደሉት” ሲል ላከባቸው። ካህኑም፣ “በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አትግደሏት” ብሎ ነበርና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ካህኑም ዮዳሄ በጭፍራው ላይ የተሾሙትን የመቶ አለቆች፦ “ከሰልፉ መካከል አውጡአት የሚከተላትም በሰይፍ ይገደል” ብሎ አዘዛቸው። ካህኑም፦ “በጌታ ቤት ውስጥ አትግደሉአት” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ዮዳሄ በበኩሉ ዐታልያ በቤተ መቅደሱ ክልል ውስጥ እንድትገደል አልፈለገም፤ ስለዚህም የጦር መኰንኖቹን ጠርቶ “ግራና ቀኝ በተሰለፉት ዘቦች መካከል አውጥታችሁ ውሰዱአት፤ እርስዋን ከሞት ለማትረፍ የሚሞክር ሰው ቢኖር ግደሉት” ሲል አዘዛቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ካህኑም ዮዳሄ በጭፍራው ላይ የተሾሙትን የመቶ አለቆች “ወደ ሰልፉ መካከል አውጡአት የሚከተላትም በሰይፍ ይገደል” ብሎ አዘዛቸው። ካህኑም “በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ አትግደሉአት” አለ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 23:14
7 Referencias Cruzadas  

የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ር​በው በፈ​ጸሙ ጊዜ ኢዩ ዘበ​ኞ​ቹ​ንና አለ​ቆ​ቹን፥ “ግቡና ግደ​ሉ​አ​ቸው፤ አን​ድም አያ​ም​ልጥ” አላ​ቸው። በሰ​ይ​ፍም ስለት ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ ዘበ​ኞ​ችና አለ​ቆ​ችም ወደ ውጭ ጣሉ​አ​ቸው፤ ወደ በዓ​ልም ቤት ከተማ ሄዱ።


ካህ​ኑም ዮዳሄ በጭ​ፍ​ራው ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን የመቶ አለ​ቆች፥ “ወደ ሰልፉ መካ​ከል አው​ጡ​አት፤ የሚ​ከ​ተ​ላ​ት​ንም በሰ​ይፍ ግደ​ሉት” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፤ ካህኑ፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አት​ገ​ደል” ብሎ​አ​ልና።


ንጉ​ሡ​ንም በዙ​ሪ​ያው ክበ​ቡት፤ የጦር ዕቃ​ች​ሁም በእ​ጃ​ችሁ ይሁን፤ በሰ​ል​ፋ​ች​ሁም መካ​ከል የሚ​ገባ ይገ​ደል፤ ንጉ​ሡም በወ​ጣና በገባ ጊዜ ከእ​ርሱ ጋር ሁኑ።”


እነ​ሆም፥ ንጉሡ በመ​ግ​ቢ​ያው በዓ​ምዱ አጠ​ገብ ሆኖ በን​ጉ​ሡም ዙሪያ አለ​ቆ​ችና መለ​ከ​ተ​ኞች፥ መኳ​ን​ን​ትም ቆመው አየች። ሕዝ​ቡም ሁሉ ደስ ብሎ​አ​ቸው መለ​ከ​ቱን ይነፉ ነበር፤ መዘ​ም​ራ​ንም በዜማ ዕቃ እያ​ዜሙ የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር ይዘ​ምሩ ነበር። ጎቶ​ል​ያም ልብ​ስ​ዋን ቀድዳ፥ “ዐመፅ ነው! ዐመፅ ነው!” ብላ ጮኸች።


ገለ​ልም ብለው አሳ​ለ​ፉ​አት፤ እር​ስ​ዋም ወደ ፈረሱ በር መግ​ቢያ ወደ ንጉሡ ቤት ሄደች፤ በዚ​ያም ገደ​ሉ​አት።


ሰው ግን ቢሸ​ምቅ ጠላ​ቱ​ንም በተ​ን​ኰል ቢገ​ድ​ለ​ውና ቢማ​ፀን፥ እን​ዲ​ገ​ደል ከመ​ሠ​ዊ​ያዬ አው​ጥ​ተህ ውሰ​ደው።


እር​ሱም፥ “ቤቱን አር​ክሱ፤ ወጥ​ታ​ችሁ ግደሉ፤ በሙ​ታ​ንም መን​ገ​ዶ​ችን ሙሉ” አላ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos