2 ዜና መዋዕል 21:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም የፍልስጥኤማውያንና በኢትዮጵያውያን አጠገብ የሚኖሩትን የዓረባውያንን የቊጣ መንፈስ በኢዮራም ላይ አስነሣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ፍልስጥኤማውያንንና በኢትዮጵያውያን አጠገብ የሚኖሩ ዐረቦችን በኢዮራም ላይ በጠላትነት እንዲነሡ አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በባሕር ዳርቻ ሰፍረው በነበሩት ኢትዮጵያውያን አጠገብ ፍልስጥኤማውያንና ዐረቦች ይኖሩ ነበር፤ እግዚአብሔርም እነርሱን በኢዮራም ላይ ጦርነት እንዲያደርጉ አነሣሣቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ፍልስጥኤማውያንንና በኢትዮጵያውያን አጠገብ የሚኖሩትን የዓረብያን ሰዎች በኢዮራም ላይ አስነሣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የፍልስጥኤማውያንና በኢትዮጵያውያን አጠገብ የሚኖሩትን የዓረባውያንን መንፈስ በኢዮራም ላይ አስነሣ። |
እንዲህም አለው፤ “ከእኔ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን ሆን ብለህ ስላፈረስክና ሕጌንም ስላልፈጸምክ፥ መንግሥትህን ከአንተ ወስጄ ከአገልጋዮችህ ለአንዱ ልሰጠው ወስኛለሁ።
እንደገናም ጌታ ረዞን ተብሎ የሚጠራውን የኤሊዓዳን ልጅ በሰሎሞን ላይ ጠላት አድርጎ አስነሣ፤ ረዞን የጾባ ንጉሥ ከነበረው ከጌታው ከሀዳድዔዜር ኮብልሎ፥
ከፍልስጥኤማውያንም ለኢዮሣፍጥ እጅ መንሻና የብር ግብር ያመጡ ነበሩ፤ ዓረባውያንም ደግሞ ከመንጎቻቸው ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ በጎችና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ ፍየሎች ያመጡለት ነበር።
በኢየሩሳሌም የነበሩትም ታናሹን ልጁን አካዝያስን በእርሱ ፋንታ አነገሡት። የመጣባቸው የዓረብና የአሊማዞን የሽፍቶች ጭፍራ የእርሱን ታላቆች ገድለዋቸው ነበርና። የይሁዳም ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ነገሠ።
በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት፥ በኤርምያስ አፍ የተናገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም፥ ጌታ የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ፥ ይህም በመንግሥቱ ሁሉ በአዋጅና በጽሑፍ እንዲያስነግር ነው፤
እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣው የይሁዳና የብንያም የአባቶች አለቆች፥ ካህናቱና ሌዋውያኑም ሁሉ ለመሄድና በኢየሩሳሌም ያለውን የጌታን ቤት ለመሥራት ተዘጋጁ።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ለኤዶምያስ አሳልፈው ለመስጠት መላውን ሕዝብ ማርከው ወስደዋልና ስለ ሦስት የጋዛ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።
አሁንም ንጉሥ ጌታዬ የባርያውን ቃል ያድምጥ፤ ጌታ በእኔ ላይ አነሣሥቶህ እንደሆነ፥ መሥዋዕት ይቀበል፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ፥ በጌታ ፊት የተረገሙ ይሁኑ፥ ‘ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ’ ብለው በጌታ ርስት ድርሻ እንዳይኖረኝ ዛሬ አሳደውኛልና።