2 ዜና መዋዕል 20:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኢዮሣፍጥም መንግሥት ጸጠጥታ ሰፈነበት፥ አምላኩም በዙርያው ካሉ አሳረፈው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላኩ በየአቅጣጫው ዕረፍት ስለ ሰጠው፣ የኢዮሣፍጥ መንግሥት ሰላም አግኝቶ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ኢዮሣፍጥ አገሪቱን በሰላም አስተዳደረ፤ እግዚአብሔርም በሁሉ አቅጣጫ የሰላም ዋስትና ሰጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢዮሣፍጥም መንግሥት ሰላም ሆነች፤ አምላኩም እግዚአብሔር በዙሪያው ካሉ አሳረፈው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢዮሣፍጥም መንግሥት ጸጥ አለች፤ አምላኩም በዙሪያው ካሉ አሳረፈው። |
በፍጹምም ልባቸው ምለዋልና፥ በፍጹምም ሕሊናቸው ፈልገውታልና፥ እርሱም ተገኝቶላቸዋልና ይሁዳ ሁሉ በመሐላው ደስ አላቸው፤ ጌታም በዙሪያቸው እረፍት ሰጣቸው።
በምድሪቱም ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ማንም ሳያስፈራራችሁ ያለ ስጋት ትተኛላችሁ፤ ክፉዎችንም አራዊት ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፥ ሰይፍም በምድራችሁ ላይ አያልፍም።
የእስራኤል ትሩፍ ኃጢአትን አይሠሩም፥ ሐሰትንም አይናገሩም፥ በአፋቸውም ውስጥ አታላይ ምላስ አይገኝም፤ እነርሱም ይሰማራሉ፥ ይተኛሉ፥ የሚያስፈራቸውም የለም።
እንዲህም ሆነ፤ ከብዙ ዘመን በኋላ፥ ጌታም እስራኤልን በዙሪያቸው ካሉት ጠላቶቻቸው ሁሉ ባሳረፋቸው ጊዜ፥ ኢያሱም በሸመገለ ዕድሜውም በገፋ ጊዜ፥