2 ዜና መዋዕል 15:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 በፍጹምም ልባቸው ምለዋልና፥ በፍጹምም ሕሊናቸው ፈልገውታልና፥ እርሱም ተገኝቶላቸዋልና ይሁዳ ሁሉ በመሐላው ደስ አላቸው፤ ጌታም በዙሪያቸው እረፍት ሰጣቸው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 በፍጹም ልባቸው ስለ ማሉም የይሁዳ ሕዝብ በመሐላው ደስ ተሠኙ። እግዚአብሔርን ከልብ ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በሁሉም አቅጣጫ ዕረፍት ሰጣቸው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 የይሁዳ ሰዎች ሁሉ በፍጹም ልባቸው ይህን ቃል ኪዳን ስለ ገቡ ደስ ተሰኝተው ነበር፤ እግዚአብሔርንም አጥብቀው ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው፤ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር በመሆን በዙሪያቸው ሁሉ ሰላም እንዲኖር አደረገላቸው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 በፍጹምም ልባቸው ምለዋልና፥ በፍጹምም ሕሊናቸው ፈልገውታልና፥ እርሱም ተገኝቶላቸዋልና ይሁዳ ሁሉ በመሐላው ደስ አላቸው፤ እግዚአብሔርም በዙሪያቸው ዕረፍትን ሰጣቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 በፍጹምም ልባቸው ምለዋልና፥ በፍጹምም ሕሊናቸው ፈልገውታልና፥ እርሱም ተገኝቶላቸዋልና ይሁዳ ሁሉ በመሐላው ደስ አላቸው፤ እግዚአብሔርም በዙሪያቸው እረፍት ሰጣቸው። Ver Capítulo |