2 ዜና መዋዕል 20:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሕዝቡም ጋር ተማክሮ በሠራዊቱ ፊት የሚሄዱትን፦ “ጽኑ ፍቅሩ ለዘዓለም ነውና ጌታን አመስግኑ” የሚሉትንም ጌጠኛ ልብስም ለብሰው የሚያመሰግኑትን፥ ለጌታም የሚዘምሩትን መዘምራን አቆመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሕዝቡም ጋራ ከተመካከረ በኋላ ከሰራዊቱ ፊት ቀድመው በመሄድ፣ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፣ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና” እያሉ ለእግዚአብሔር የሚዘምሩና ስለ ቅድስናውም ክብር የሚያወድሱ ሰዎችን መደበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ከሕዝቡ ጋር ከተመካከረ በኋላ መዘምራኑ በተቀደሱ በዓላት የሚለብሱአቸውን ካባዎች ለብሰው “ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ!” እያሉ በመዘመር በሠራዊቱ ፊት ለፊት እንዲያልፉ አዘዘ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሕዝቡም ጋር ተማክሮ በሠራዊቱ ፊት የሚሄዱትን፥ “ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ” የሚሉትንም፥ በቅድስና የሚያመሰግኑትን፥ ለእግዚአብሔርም የሚዘምሩትን መዘምራን አቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሕዝቡም ጋር ተማክሮ በሠራዊቱ ፊት የሚሄዱትን “ምሕረቱ ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤” የሚሉትን፥ ጌጠኛ ልብስ ለብሰው የሚያመሰግኑትን፥ ለእግዚአብሔር የሚዘምሩትን መዘምራንን አቆመ። |
ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና ጌታን እንዲያመሰግኑ ኤማንንና ኤዶታምን፥ በስማቸውም የተጻፉትን ተመርጠው የቀሩትን ከእነርሱ ጋር በዚያ ተዋቸው።
በኢየሩሳሌምም ተገኝተው የነበሩ የእስራኤል ልጆች የቂጣውን በዓል በታላቅ ደስታ ሰባት ቀን አከበሩ፤ ሌዋውያኑና ካህናቱም በዜማ ዕቃ ለጌታ እየዘመሩ ዕለት ዕለት ጌታን ያመሰግኑ ነበር።
መለከቱንም የሚነፉ መዘምራኑም በአንድነት ሆነው በአንድ ድምፅ ጌታን እያመሰገኑና እያከበሩ፦ “ጌታ መልካም ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና” ጌታን አመስግኑ እያሉ ድምጻቸውን ወደ ላይ ከፍ አድርገው በመለከትና በጸናጽል በዜማም ዕቃ ሁሉ ጌታን ባመሰገኑ ጊዜ፥ ደመናው ቤቱን፥ የጌታን ቤት ሞላው።
የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወርድ የጌታም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር፤ በወለሉም ላይ በግምባራቸው ወደ ምድር ተደፍተው ሰገዱ እንዲህም ብለው ጌታን አመሰገኑ፦ “እርሱ መልካም ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና።”
ካህናቱም በየሥርዓታቸው፥ ሌዋውያኑም ደግሞ፦ ጽኑ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና ጌታን አመስግኑ የሚለውን የዳዊትን መዝሙር እየዘመሩ፥ ንጉሡ ዳዊት ጌታን ለማመስገን የሠራውን የጌታን የዜማ ዕቃ ይዘው ቆመው ነበር፤ ካህናቱም በፊታቸው መለከት ይነፉ ነበር፤ እስራኤልም ሁሉ ቆመው ነበር።
የኢየሩሳሌም ቅጥር ሲመረቅ ምረቃውን በደስታ፥ በምስጋና፥ በመዝሙር፥ በጸናጽል፥ በበገናና በክራር ለማክበር ሌዋውያኑን ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት በየሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ ፈለጉ።
እርሱም፦ የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የሙሽራው ድምፅና የሙሽራይቱ ድምፅ፥ ወደ ጌታም ቤት፦ ‘ጌታ ቸር ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና የሠራዊት ጌታን አመስግኑ!’ እያሉ የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡ ሰዎች ድምፅ ነው። የምድሪቱን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፥ ይላል ጌታ።