La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 18:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የክንዓና ልጅ ሰዴቅያስም የብረት ቀንዶች ሠርቶ፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ሶሪያውያንን እስኪጠፉ ድረስ በእነዚህ ትወጋቸዋለህ’ ” አለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ፣ የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስ የብረት ቀንዶች ሠርቶ፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ሶርያውያን እስኪጠፉ ድረስ በእነዚህ ትወጋቸዋለህ’ ” አለ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከእነርሱም አንዱ የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ከብረት ቀንዶችን ሠርቶ አክዓብን “እግዚአብሔር ‘በእነዚህ ቀንዶች ሶርያውያንን ወግተህ ፍጹም የሆነ ድልን ትቀዳጃለህ’ ይልሃል” አለው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የካ​ህ​ናን ልጅ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም የብ​ረት ቀን​ዶች ሠርቶ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሶር​ያ​ው​ያ​ንን እስ​ክ​ታ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ በእ​ነ​ዚህ ትወ​ጋ​ለህ” አለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የክንዓና ልጅ ሰዴቅያስም የብረት ቀንዶች ሠርቶ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ሶሪያውያንን እስኪጠፉ ድረስ በእነዚህ ትወጋለህ’” አለ።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 18:10
15 Referencias Cruzadas  

ከእነርሱም አንዱ ሴዴቅያስ ተብሎ የሚጠራው የከናዕና ልጅ ከብረት የተሠሩ ቀንዶችን ይዞ አክዓብን “ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘ከብረት በተሠሩ በእነዚህ ቀንዶች ሶርያውያንን ወግተህ ፍጹም የሆነ ድልን ትቀዳጃለህ’” አለው።


ነቢያትም ሁሉ፦ “ጌታ በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ወደ ሬማት ዘገለዓድ ሂድ፥ ለአንተም ይከናወንልሃል” እያሉ ተመሳሳይ የሆነን ትንቢት ይናገሩ ነበር።


የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ልብሰ መንግሥት ለብሰው በሰማርያ በር መግቢያ አጠገብ በአደባባይ በዙፋኖቻቸው ላይ ተቀምጠው ነበር፤ ነቢያትም ሁሉ በፊታቸው ትንቢትን ይናገሩ ነበር።


ለሚንቁኝ ሁልጊዜ፦ ጌታ፦ ሰላም ይሆንላችኋል ብሏል ይላሉ፤ በልቡም እልከኝነት ለሚሄድ ሁሉ፦ ክፉ ነገር አያገኛችሁም ይላሉ።


እኔ ሳልልካቸው እነዚህ ነቢያት ሮጡ፤ እኔም ሳልነግራቸው ትንቢትን ተናገሩ።


“አለምሁ አለምሁ” እያሉ በስሜ ትንቢትን በሐሰት የሚናገሩትን የነቢያትን ነገር ሰምቻለሁ።


እነሆ፥ ከምላሳቸው ትንቢትን አውጥተው፦ “እርሱ ይላል” በሚሉ ነቢያት ላይ ነኝ፥ ይላል ጌታ።


ጌታ እንዲህ አለኝ፦ ጠፍርንና ቀንበርን ሥራ በአንገትህም ላይ አድርግ፤


‘በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ስለሚነግሩአችሁ፥ ስለ ቆላያ ልጅ ስለ አክዓብና ስለ መዕሤያ ልጅ ስለ ሴዴቅያስ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፥ በዐይኖቻችሁም ፊት ይገድላቸዋል።


እኔ ሳልናገር፦ ጌታ እንዲህ ብሏል ስትሉ፥ ከንቱ ራእይን አላያችሁምን፥ ውሸተኛንም ምዋርት አልተናገራችሁምን?


ነቢዮችዋ ጌታ ሳይናገር “ጌታ እንዲህ ይላል” እያሉ የሐሰት ራእይ በማየትና በውሸት ሟርት፥ በኖራ ይለቀልቋቸዋል።


ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው በእምነትም ረገድ ተፈትነው የወደቁ ሰዎች ሆነው እውነትን ይቃወማሉ።