La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 13:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢዮርብዓምም ከዚያ በኋላ በአብያ ዘመን አልበረታም፤ ጌታም ቀሰፈው፥ ሞተም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢዮርብዓም በአብያ ዘመን እንደ ገና ሊያንሰራራ አልቻለም፤ ከዚያም እግዚአብሔር ስለ ቀሠፈው ሞተ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚያም በኋላ ኢዮርብዓም በአቢያ ዘመነ መንግሥት ኀይሉን ሊያንሠራራ አልቻለም፤ በመጨረሻም እግዚአብሔር በሞት ቀሠፈው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ከዚያ በኋላ በአ​ብያ ዘመን አል​በ​ረ​ታም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀሠ​ፈው፤ ሞተም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢዮርብዓምም ከዚያ በኋላ በአብያ ዘመን አልበረታም፤ እግዚአብሔርም ቀሰፈው፤ ሞተም።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 13:20
9 Referencias Cruzadas  

ኢዮርብዓም ንጉሥ ሆኖ ኻያ ሁለት ዓመት ከገዛ በኋላ ሞቶ ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ልጁ ናዳብ ተተክቶ ነገሠ።


ኢዮርብዓም በእስራኤል ላይ በነገሠ በሃያኛው ዓመት አሳ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ።


አብያም ኢዮርብዓምን አሳደደው፥ ከእርሱም ከተሞቹን፥ ቤቴልንና መንደሮችዋን፥ ይሻናንና መንደሮችዋን፥ ዔፍሮንንና መንደሮችዋን ወሰደ።


አብያም ጸና፥ ዐሥራ አራትም ሚስቶች አገባ፥ ሀያ ሁለትም ወንዶች ልጆችንና ዐሥራ ስድስት ሴቶች ልጆች ወለደ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ የዐይንህን ምኞት በቅፅበት እወስድብሃለሁ፤ ቢሆንም ግን ዋይታ አታሰማ፥ አታልቅስ፥ እንባህንም አታፍስስ።


ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያንጊዜ የጌታ መልአክ መታው፤ በትልም ተበልቶ ሞተ።


ዐሥር ቀን ያህል ካለፈ በኋላ፥ ጌታ ናባልን ቀሠፈው፤ እርሱም ሞተ።


ሕያው ጌታ አለ፥ ጌታ ራሱ ይቀሥፈዋል፤ ወይም የመሞቻው ቀን ይመጣል፤ ወይም በጦርነት ይሞታል፤ ይጠፋልም።