2 ዜና መዋዕል 1:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥበብንና እውቀትን ሰጥቼሃለሁ፤ ከአንተ በፊትም ከነበሩት ከአንተም በኋላ ከሚነሡት ነገሥታት አንድም እንኳ የሚመስልህ እንዳይኖር አድርጌ ባለጠግነትንና ሀብትን ክብርንም እሰጥሃለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥበብና ዕውቀት ይሰጥሃል፤ እንዲሁም ከአንተ በፊት የነበረ ማንኛውም ንጉሥ ያላገኘውን፣ ከአንተ በኋላም የሚነሣው የማያገኘውን ብልጽግና፣ ሀብትና ክብር እሰጥሃለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እነሆ የጠየቅኸውን ጥበብና ዕውቀት እሰጥሃለሁ፤ በተጨማሪም ከዚህ በፊት ማንም ንጉሥ ካገኘውና ወደፊትም ማንም ሊያገኘው ከሚችለው የሚበልጥ ብልጽግና፥ ሀብትና ዝና እሰጥሃለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥበብንና ማስተዋልን እሰጥሃለሁ። ካንተ በፊት ለነበሩ ነገሥታት ያልተሰጠውን፥ ከአንተም በኋላ ለሚነሡ የማይሰጠውን ብልፅግናን፥ ገንዘብንና ክብርን እሰጥሃለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጥበብንና እውቀትን ሰጥቼሃለሁ፤ ከአንተ በፊትም ከነበሩት ከአንተም በኋላ ከሚነሡት ነገሥታት አንድ ስንኳ የሚመስልህ እንዳይኖር ባለጠግነትንና ሀብትን ክብርንም እሰጥሃለሁ፤” አለው። |
ባለጠግነትና ክብር ከአንተ ዘንድ ነው፥ አንተም ሁሉን ትገዛለህ፤ ኃይልና ብርታት በእጅህ ነው፤ ታላቅ ማድረግ፥ ለሁሉም ኃይልን መስጠት በእጅህ ነው።
የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን በዚህ ነገር ኃጢአት አድርጎ የለምን? በብዙ አሕዛብም መካከል እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ አልነበረም፥ በአምላኩም ዘንድ የተወደደ ነበረ፥ እግዚአብሔርም በእስራኤል ሁሉ ላይ አንግሦት ነበር፥ እርሱንም እንኳ እንግዶች ሴቶች አሳቱት።