1 ዜና መዋዕል 29:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ባለጠግነትና ክብር ከአንተ ዘንድ ነው፥ አንተም ሁሉን ትገዛለህ፤ ኃይልና ብርታት በእጅህ ነው፤ ታላቅ ማድረግ፥ ለሁሉም ኃይልን መስጠት በእጅህ ነው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ባለጠግነትና ክብር የሚገኘው ከአንተ ነው፤ አንተም የሁሉ ገዥ ነህ፤ ከፍ ከፍ ለማድረግ፣ ለሁሉም ብርታትን ለመስጠት፣ ብርታትና ኀይል በእጅህ ነው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ብልጽግናና ክብር ሁሉ የሚገኘው ከአንተ ነው፤ አንተ ሁሉን ትገዛለህ፤ ኀይልና ብርታት ያንተ ናቸው፤ የወደድከውንም ታላቅና ብርቱ ማድረግ ይቻልሃል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ባለጠግነትና ክብር ከአንተ ዘንድ ነው፤ አቤቱ፥ አንተም ሁሉን ትገዛለህ፤ የሥልጣን ሁሉ ጌታ ነህ፤ ኀይልና ብርታት በእጅህ ነው፤ ኀያል ነህ፤ ታላቅ ለማድረግ፥ ለሁሉም ኀይልን ለመስጠት ዓለምን ሁሉ በእጅህ የያዝህ ነህ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ባለጠግነትና ክብር ከአንተ ዘንድ ነው፥ አንተም ሁሉን ትገዛለህ፤ ኀይልና ብርታት በእጅህ ነው፤ ታላቅ ለማድረግ፥ ለሁሉም ኀይልን ለመስጠት በእጅህ ነው። Ver Capítulo |