መክብብ 5:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 እግዚአብሔር በልቡ ደስታን እስካኖረ ድረስ፥ እርሱ የሕይወቱን ዘመን እጅግም አያስብም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 አምላክ ለሰው ባለጠግነትና ሀብት መስጠቱ፣ እንዲደሰትበትም ማስቻሉ፣ ዕጣውን እንዲቀበልና በሥራውም እንዲደሰት ማድረጉ፣ ይህ የአምላክ ስጦታ ነው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 እግዚአብሔር ለሰው ሀብትና ብልጽግናን መስጠቱ የደከመበትን ድርሻ አግኝቶ በመብላትና በመጠጣት ደስ እንዲለው ፈቅዶለት ነው፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ባለጠግነትንና ሀብትን መስጠቱ፥ ከእርስዋም ይበላና ዕድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ፥ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ማሠልጠኑ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ባለጠግነትንና ሀብትን መስጠቱ፥ ከእርስዋም ይበላና እድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ማሠልጠኑ፥ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። Ver Capítulo |