1 ጢሞቴዎስ 6:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑትን ሰዎች እንዳይታበዩ በሚያልፍም ባለጠግነት ላይ ሳይሆን እንድንደሰትበት ሁሉን አትረፍርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንዲያደርጉ እዘዛቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ዓለም ባለጠጎች የሆኑት እንዳይታበዩ፣ ደስም እንዲለን ሁሉን ነገር አትረፍርፎ በሚሰጠን በእግዚአብሔር እንጂ አስተማማኝነት በሌለው በሀብት ላይ ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዚህ ዓለም ሀብታሞች እንዳይታበዩ ወይም ተስፋቸውን አስተማማኝ ባልሆነ ሀብት ላይ እንዳያደርጉ እዘዛቸው፤ እንዲሁም ተስፋቸው እኛን ደስ እንዲለን ሁሉን ነገር አትረፍርፎ በሚሰጠን በእግዚአብሔር ላይ እንዲሆን እዘዛቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ፥ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው። |
ትውልድ ሆይ! የጌታን ቃል ተመልከቱ። በውኑ ለእስራኤል ምድረ በዳ ወይስ የጨለመች ምድር ሆንኩባትን? ሕዝቤስ ስለምን፦ ‘እኛ ፈርጥጠናል፤ ዳግመኛ ወደ አንተ አንመጣም’ ይላሉ?
ማን በእኔ ላይ ይመጣብኛል ብለሽ በመዝገብሽ የታመንሽ አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ! በሸለቆችሽ፥ ውኃ በሚፈስስባቸው ሸለቆችሽ፥ ለምን ትመኪያለሽ?
በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ ግን በዚህ ዓለምም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።
ደቀ መዛሙርቱም በንግግሩ ተገረሙ፤ ኢየሱስ ግን እንደገና መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ልጆች ሆይ፤ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ከባድ ነገር ነው፤
ከዚህም ሁሉ ጋር መልካም ሥራ እየሠራ፥ ከሰማይ ዝናብን ፍሬ የሚሆንበትንም ወራት ሲሰጠን፥ ልባችንንም በመብልና በደስታ ሲሞላው ራሱን ያለ ምስክር አልተወም።”
በደረሱም ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ ለአሕዛብም የሃይማኖትን ደጅ እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ።
የክርስቶስ ቃል በሙላት በእናንተ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩም፤ በመዝሙርና በውዳሴ በመንፈሳዊም ዝማሬ በልባችሁ በማመስገን ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤
እነርሱ ራሳቸው ስለ እኛ በእናንተ መካከል ምን ዓይነት አቀባበል ተደርጎልን እንደ ነበር፥ ሕያውም የሆነውን እውነተኛ አምላክ ለማገልገል ከጣዖታት ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንደተመለሳችሁ፥
ይህ ሳይሆን ቀርቶ ብዘገይ ግን፥ በዚህ በጻፍሁልህ ትእዛዝ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ የእውነት ዓምድና መሠረት በሆነችው በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ እንድታውቅ ነው።
አንዱን ከሌላው በማበላለጥ ምንም ዓይነት ነገር ሳታደርግ፥ ያለ አድልዎ እነዚህን ትዛዛቶች እንድትጠብቅ በእግዚአብሔርና በጌታ በክርስቶስ ኢየሱስ በተመረጡትም መላእክት ፊት አደራ እልሃለሁ።
ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ለመሆን የሚፈልጉ በፈተናና በወጥመድ፥ ሰዎችንም በጉስቁልናና በጥፋት ወስጥ በሚያሰጥሙአቸው ከንቱና ጎጂ በሆኑ በብዙ ምኞቶች ይወድቃሉ።
ይህም ጸጋ፥ ኀጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን ራሳችንን በመቈጣጠርና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ይመክረናል፤