Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ጢሞቴዎስ 4:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ለዚህም እንደክማለን እንታገላለንም፤ ምክንያቱም ሰውን ሁሉ በተለይም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስላደረግን ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ለዚህ ብለን እንጥራለን፤ እንደክማለንም፤ ይኸውም ለሰዎች ሁሉ፣ በተለይም ለሚያምኑት አዳኝ በሆነው በሕያው እግዚአብሔር ተስፋ ስለምናደርግ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እኛ ሰዎችን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን ሁሉ በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ የምናደርግ ስለ ሆነ በሥራ እንደክማለን፤ እንታገላለን።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ይህን ለማግኘት እንደክማለንና፤ ስለዚህም እንሰደባለን፤ ይህም ሰውን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ይህን ለማግኘት እንደክማለንና፥ ስለዚህም እንሰደባለን፤ ይህም ሰውን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው።

Ver Capítulo Copiar




1 ጢሞቴዎስ 4:10
40 Referencias Cruzadas  

እርሱም ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲመጡ ፈቃዱ የሆነ አምላክ ነው።


እርሱም የኃጢአታችን ማስተስረያ ነው፥ ለእኛ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።


ራሱንም ለሁሉ ቤዛ አድርጎ ሰጠ፤ ይህም ምስክርነት ተገቢ በሆነው በራሱ ጊዜ የቀረበ ነበር፤


በማግሥቱ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ “እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።


አብ ወልድን የዓለም አዳኝ እንዲሆን እንደ ላከው አይተናል፥ እንመሰክራለንም።


ሴቲቱንም “አሁን የምናምነው በቃልሽ ምክንያት አይደለም፤ እኛ እራሳችን ሰምተነዋልና፤ እርሱ በእውነት የዓለም መድኃኒት እንደሆነ እናውቃለን፤” ይሉአት ነበር።


እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።


ጌታ አምላክ ፀሐይና ጋሻ ነው፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፥ ጌታ በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያስቀራቸውም።


ስለዚህ እኛም እርሱ የተሸከ መውን ውርደት ተሸክመን ከሰፈር ውጭ ወደ እርሱ እንውጣ።


እነሆ፤ ጌታ መዳኛዬ ነው፤ እታመናለሁ፤ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ የመዳኔ ምክንያትም ሆኖአል።”


በሰው ከመታመን ይልቅ በጌታ መጠለል ይሻላል።


ጻድቃን አይተው ይፈራሉ፥ በእርሱም ይሥቃሉ እንዲህም ይላሉ፦


እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፥ ከሞት ባስነሣው ክብርንም በሰጠው፥ በእግዚአብሔር በእርሱ ትተማመናላችሁ።


ወደ ፊት የሚቀበለውን ብድራት ከሩቅ ተመልክቶአልና፥ ከግብጽ ሀብት ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ሀብት መሆኑን ተገነዘበ።


በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑትን ሰዎች እንዳይታበዩ በሚያልፍም ባለጠግነት ላይ ሳይሆን እንድንደሰትበት ሁሉን አትረፍርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንዲያደርጉ እዘዛቸው።


ይህ ሳይሆን ቀርቶ ብዘገይ ግን፥ በዚህ በጻፍሁልህ ትእዛዝ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ የእውነት ዓምድና መሠረት በሆነችው በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ እንድታውቅ ነው።


በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ብሏልና የሚወደው ከሆነ እስቲ አሁን ያድነው።”


ጌታ መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ የሚሸሸጉትን ያውቃል።


በጌታ የታመነ ጌታም መተማመኛው የሆነ ሰው ቡሩክ ነው።


ከእናንተ ጌታን የሚፈራ፥ የአገልጋዩንም ቃል የሚሰማ፥ በጨለማም የሚሄድ፥ ብርሃንም የሌለው፥ ነገር ግን በጌታ ስም የሚታመን፥ በአምላኩም የሚደገፍ ማን ነው?


ጌታ የታደጋቸው፥ ከጠላትም እጅ ያዳናቸው ይናገሩ።


ጌታ ይረዳቸዋል፥ ያድናቸዋልም፥ ከከፉዎችም እጅ ያወጣቸዋል፥ ያድናቸዋልም፥ በእርሱ ታምነዋልና።


አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህ በሰማይ ነው፥ ታማኝነትህም ወደ ደመናት ትደርሳለች።


ስምዖን ጴጥሮስም “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብሎ መለሰ።


ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን የሆንሁትን ሆኛለሁ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋ ከንቱ አልሆነም፤ ይልቁን ከሁሉም በላይ በትጋት ሠርቻለሁ፤ ሆኖም ግን እኔ ሳልሆን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው።


እርሱ እንዲህ ካለው የሞት አደጋ አድኖናል፤ ያድነናልም፤ ወደፊትም ደግሞ እንደሚያድነን ተስፋችንን በእርሱ ላይ ጥለናል።


ይህም በአዳኛችን በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios