1 ሳሙኤል 5:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሽዶድ ሰዎች ይህን ባዩ ጊዜ፥ “እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ጠንክሯልና የእስራኤል አምላክ ታቦት በእኛ ዘንድ መቆየት የለበትም” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሽዶድ ሰዎች ይህን ባዩ ጊዜ፣ “እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ጠንክሯልና የእስራኤል አምላክ ታቦት በእኛ ዘንድ መቈየት የለበትም” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአሽዶድ ኗሪዎች የሆነውን ነገር ሁሉ ባዩ ጊዜ “ቊጣው በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ስለ በረታ የእስራኤል አምላክ ታቦት እዚህ እኛ ዘንድ መቈየት የለበትም” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአዛጦንም ሰዎች እንዲህ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ፥ “እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ጠንክራለችና የእስራኤል አምላክ ታቦት ከእኛ ዘንድ አትቀመጥ” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአዛጦንም ሰዎች እንዲህ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ፦ እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ጠንክራለችና የእስራኤል አምላክ ታቦት ከእኛ ዘንድ አይቀመጥ አሉ። |
የፈርዖንም አገልጋዮች፦ “ይህ ሰው እስከ መቼ ወጥመድ ይሆንብናል? ጌታ አምላካቸውን እንዲያገለግሉት ወንዶቹን ልቀቃቸው፥ ግብጽስ እንደ ጠፋች ገና አላወቅህምን?” አሉት።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ የኖእ አሞንን፥ ፈርዖንንም፥ ግብጽንም፥ አማልክቶችዋንና ነገሥታቶችዋንም፥ ፈርዖንና በእርሱም የሚታመኑትን እቀጣለሁ፤
ከዚህ በኋላ የፍልስጥኤማውያንን ገዢዎች በሙሉ ጠርተው፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ምን እናድርገው?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወደ ጋት ውሰዱት” አሏቸው። ስለዚህ የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወሰዱት።