Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 12:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ግብፃውያንም ፈጥነው ከምድሩ እንዲወጡ ሕዝቡን ያስቸኩሉአቸው ነበር፥ “ሁላችንም ልንሞት ነው” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ግብጻውያን አገራቸውን በአስቸኳይ ለቅቀው እንዲወጡላቸው እስራኤላውያንን አጣደፏቸው። “አለዚያማ ሁላችንም ማለቃችን ነው” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 አገሪቱን ለቀውላቸው እንዲወጡ ግብጻውያን ራሳቸውም ሕዝቡን በማጣደፍ “በአስቸኳይ ለቃችሁ ካልወጣችሁልን እነሆ ሁላችንም ማለቃችን ነው” አሉአቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ፈጥ​ነው ከም​ድሩ ይወጡ ዘንድ ሕዝ​ቡን ያስ​ቸ​ኩ​ሉ​አ​ቸው ነበር፥ “ሁላ​ች​ንም እን​ሞ​ታ​ለን” ብለ​ዋ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ግብፃውያንም ፈጥነው ከምድሩ ይወጡ ዘንድ ሕዝቡን ያስቸኵሉአቸው ነበር፤ “ሁላችን እንሞታለን” ብለዋልና።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 12:33
9 Referencias Cruzadas  

ፈርተዋቸው ነበርና ግብጽ በመውጣታቸው ደስ አላት።


ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በፈርዖንና በግብጽ ላይ ገና አንድ መቅሰፍት አመጣለሁ፥ ከዚያ በኋላ ከዚህ ይለቅቃችኋል፤ ሲለቅቃችሁም ሙሉ በሙሉ ያባርራችኋል።


እግዚአብሔርም ሌሊት በሕልም ወደ አቢሜሌክ መጣ፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰድሃት ሴት ትሞታለህ፤ እርሷ ባለ ባል ናትና” አለው።


ጌታም ሙሴን አለው፦ “አሁን ፈርዖንን ምን እንደማደርገው ታያለህ በጸናች እጅ ይለቅቃቸዋል፥ በጸናችም እጅ ከምድሩ አስወጥቶ ይሰድዳቸዋል።”


የፈርዖንም አገልጋዮች፦ “ይህ ሰው እስከ መቼ ወጥመድ ይሆንብናል? ጌታ አምላካቸውን እንዲያገለግሉት ወንዶቹን ልቀቃቸው፥ ግብጽስ እንደ ጠፋች ገና አላወቅህምን?” አሉት።


ከግብጽም ከእነርሱ ጋር ያወጡትን ሊጥ ጋገሩ፥ አልቦካም ነበርና ቂጣ አደረጉት፤ ግብፃውያን በመውጣት ስላስቸኮሉአቸው ይቆዩ ዘንድ አልተቻላቸውም፥ ስንቅም አላሰናዱም ነበር።


ጌታ ቀድሟችሁ ያልፋልና፥ የእስራኤልም አምላክ ይከተላችኋልና በችኮላ አትወጡም፤ በመኮብለልም አትሄዱም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios