1 ሳሙኤል 30:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት፥ ከዚያች እለት ምሽት ጀምሮ እስከ ማግሥቱ ምሽት ድረስ ወጋቸው፤ በግመል ተቀምጠው ከሸሹት አራት መቶ ወጣቶች በስተቀር፥ ከመካከላቸው ያመለጠ አንድም አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት፣ ከዚያች ዕለት ማታ ጀምሮ እስከ ማግስቱ ምሽት ድረስ ወጋቸው፤ በግመል ተቀምጠው ከሸሹት አራት መቶ ወጣቶች በቀር፣ ከመካከላቸው ያመለጠ አንድም አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምሽት ጊዜ ዳዊት በእነርሱ ላይ አደጋ ጥሎ እስከ ማግስቱ ማታ ድረስ ተዋጋቸው፤ በግመል ላይ ተቀምጠው እየጋለቡ ከሸሹት አራት መቶ ወጣቶች በስተቀር ከነዚያ ወራሪዎች ያመለጠ አንድም አልነበረም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ሄዶ የአጥቢያ ኮከብ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ዳግመኛም በማግሥቱ መታቸው፤ ከእነርሱም በግመል ተቀምጠው ከሸሹት አራት መቶ ጐልማሶች በቀር አንድም ያመለጠ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ከማታ ጀምሮ እስከ ማግሥቱ ማታ ድረስ መታቸው፥ ከእነርሱም በግመል ተቀምጠው ከሸሹ ከአራት መቶ ጕልማሶች በቀር አንድ ያመለጠ የለም። |
የገበሩትም መንግሥታት ኤዶምና ሞዓብ፥ አሞናውያን፥ ፍልስጥኤማውያንና አማሌቃውያን ነበሩ። እንዲሁም ከጾባ ንጉሥ ከረሖብ ልጅ ከሀዳድዔዜር የወሰደውን ምርኮ ለጌታ ቀደሰ።
ባራቅ ግን የሲሣራን ሠረገሎችና ሠራዊቱን እስከ ሐሮሼት ሐጎይም ድረስ አሳደዳቸው፤ የሲሣራ ሠራዊት በሙሉ በሰይፍ ወደቀ፤ በሕይወት የተረፈ አንድም ሰው አልነበረም።
ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ምድያማውያን፥ አማሌቃውያንና ሌሎችም የምሥራቅ ሕዝቦች በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ የግመሎቻቸውም ብዛት በባሕር ዳርቻ እንዳለ አሸዋ ስፍር ቍጥር አልነበረውም።
በማግስቱ ሳኦል ሠራዊቱን ከሦስት ቦታ ከፈለው፤ ሊነጋጋ ሲል የአሞናውያንን ሰፈር ጥሰው በመግባት ፀሓይ ሞቅ እስኪል ድረስ ፈጇቸው። በሕይወት የተረፉትም ሁለት እንኳን ሆነው በአንድ ላይ ሊሆኑ እስከማይችሉ ድረስ ተበታተኑ።
አሁንም ሂድ፤ አማሌቃውያንን ውጋ፤ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፤ አንዱንም አታስቀር፤ ወንዱንም ሴቱንም፥ ልጁንም ሕፃኑንም፥ የቀንድ ከብቱንም በጉንም፥ ግመሉንም አህያውንም ግደል።’ ”