ዖዛ በድፍረት ይህን ስላደረገ፥ የጌታ ቁጣ በላዩ ላይ ነደደ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ቀሠፈው፤ እርሱም በእግዚአብሔር ታቦት አጠገብ እዚያው ሞተ።
1 ሳሙኤል 25:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐሥር ቀን ያህል ካለፈ በኋላ፥ ጌታ ናባልን ቀሠፈው፤ እርሱም ሞተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐሥር ቀን ያህል ካለፈ በኋላ፣ እግዚአብሔር ናባልን ቀሠፈው፤ እርሱም ሞተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዐሥር ቀኖች በኋላም እግዚአብሔር ስለ ቀሠፈው ናባል ሞተ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዐሥር ቀንም በኋላ እግዚአብሔር ናባልን ቀሠፈው፤ እርሱም ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ድንጋይም ሆነ፥ ከአሥር ቀንም በኋላ እግዚአብሔር ናባልን ቀሠፈው፥ እርሱም ሞተ። |
ዖዛ በድፍረት ይህን ስላደረገ፥ የጌታ ቁጣ በላዩ ላይ ነደደ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ቀሠፈው፤ እርሱም በእግዚአብሔር ታቦት አጠገብ እዚያው ሞተ።
በኋላም እግዚአብሔር በዖዝያ ላይ የቆዳ በሽታ አሳደረበት፤ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ይህ በሽታ ስላልለቀቀው ከሥራው ሁሉ ተገልሎ በተለየ ቤት ውስጥ ለብቻው ይኖር ነበር፤ በዚህም ጊዜ መንግሥቱን ሲመራ የቆየው ልጁ ኢዮአታም ነበር።
በዚያው ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ አሦራውያን ሰፈር አልፎ አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ወታደሮችን ገደለ፤ በማግስቱ በማለዳ ሰዎች በሚነቁበት ጊዜ ሁሉም ሞተው ተገኙ።
ጌታም በሴሎናዊው በአሒያ አድርጎ ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረውን ቃል እንዲያጸና ከጌታ ዘንድ ተወስኖ ነበርና ንጉሡ ሕዝቡን አልሰማም።
እንዲህም ሆነ እኩለ ሌሊት ላይ ጌታ በግብጽ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ፥ በዙፋን ከተቀመጠው ከፈርዖን በኩር ጀምሮ በእስር ቤት እስካሉት እስከ እስረኞች በኩር ድረስ፥ የከብቶችንም በኩር ሁሉ መታ።
ከዚያም ወዴት እንደሚሄድ ተመልከቱ፤ ወደ ገዛ አገሩ ወደ ቤትሼሜሽ አቅጣጫ የሚሄድ ከሆነ፥ ይህን ታላቅ መከራ ያመጣብን እርሱ ነው። ወደዚያ ካልሄደ ግን፥ መከራው በአጋጣሚ የደረሰብን እንጂ የእርሱ እጅ እንዳልመታን እናውቃለን።”