1 ሳሙኤል 23:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ መልእክተኛ ወደ ሳኦል መጥቶ፥ “ፍልስጥኤማውያን አገሩን ወረውታልና ቶሎ ድረስ!” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ መልእክተኛ ወደ ሳኦል መጥቶ፣ “ፍልስጥኤማውያን አገሩን ወረውታልና ቶሎ ድረስ!” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ በዚህ እንዳለ ወዲያውኑ አንድ መልእክተኛ ደርሶ ሳኦልን “ፍልስጥኤማውያን አገሪቱን በመውረር ላይ ናቸውና አሁኑኑ ፈጥነህ ተመልሰህ ና!” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሳኦልም መልእክተኛ መጥቶ፥ “ፍልስጥኤማውያን ሀገሩን ወርረውታልና ፈጥነህ ና” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሳኦልም መልእክተኛ መጥቶ፦ ፍልስጥኤማውያን አገሩን ወርረውታልና ፈጥነህ ና አለው። |
በኢትዮጵያ ንጉሥ በቲርሃቃ የሚመራ የግብጽ ሠራዊት እነርሱን ለመውጋት በመገሥገሥ ላይ መሆኑን አሦራውያን ሰሙ፤ ወዲያውኑ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ በመልእክተኞች እጅ ላከ፦
ሳኦል በተራራው በአንዱ በኩል ሆኖ ሲያሳድድ፥ ዳዊትና ሰዎቹ ደግሞ በተራራው በሌላ በኩል ከሳኦል ለማምለጥ ይጣደፉ ነበር። ሳኦልና ወታደሮቹ ዳዊትንና ሰዎቹን ከበው ለመያዝ ተቃርበው ሳሉ፥
አኪሽም፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” ሲል በጠየቀው ጊዜ ዳዊት፥ “የዘመትነው በይሁዳ፥ ወይም በይራሕመኤላውያን፥ ወይም በቄናውያን ላይ ነው” እያለ ይመልስለት ነበር።