La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 23:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አሁንም ንጉሥ ሆይ፤ አንተ ደስ ባለህ ጊዜ ናና፥ እርሱን ለንጉሡ አሳልፎ መስጠት የእኛ ድርሻ ነው” አሉት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሁንም ንጉሥ ሆይ፤ አንተ ደስ ባለህ ጊዜ ና እንጂ፣ እርሱን ለንጉሡ አሳልፎ ለመስጠት እኛ አለን።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ንጉሥ ሆይ፥ አንተ እርሱን በምትፈልግበት ጊዜ ወደ እኛ ና፤ እኛም እርሱን ለአንተ ለንጉሡ አሳልፈን ለመስጠት ኀላፊነትን እንወስዳለን።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አሁ​ንም፦ ንጉሥ ሆይ! ለመ​ው​ረድ ፈቃ​ድህ ከሆነ ወደ እኛ ውረድ፤ በን​ጉሡ እጅ ጥሎ​ታ​ልና።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አሁንም፥ ንጉሥ ሆይ፥ ትወርድ ዘንድ ነፍስህ እንደ ወደደች ውረድ፥ በንጉሡም እጅ እርሱን አሳልፎ ለመስጠት እኛ አለን አሉት።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 23:20
11 Referencias Cruzadas  

ከዚያም አበኔር ዳዊትን፥ “ለጌታዬ ለንጉሡ መላውን እስራኤልን ልሰብስብ፥ ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን እንዲያደርጉ፥ ልብህ እንደተመኘውም ሁሉን እንድትገዛ ፈጥኜ ልሂድ” አለው። ስለዚህ ዳዊት አበኔርን አሰናበተው፤ በሰላምም ሄደ።


ክፉ ሰውም አይቶት ይቈጣል፥ ጥርሱንም ያፋጫል፥ ይቀልጣልም፥ የክፉዎች ምኞት ትጠፋለች።


አቤቱ፥ በስምህ አድነኝ፥ በኃይልህም ፍረድልኝ።


የጻድቃን ምኞት በጎ ብቻ ነው፥ የክፉዎች ተስፋ ግን መቅሠፍት ነው።


እንደ ክፉ ሰው በጻድቅ ቤት ላይ አትሸምቅ፥ ማደሪያውንም አታውክ።


ብዙ ሰዎች የሹምን ፊት ይሻሉ፥ የሰው ፍርድ ግን ከጌታ ዘንድ ነው።


“በእስራኤል ካሉት ከተሞችህ መካከል፥ አንድ ሌዋዊ ከሚኖርበት ከየትኛውም በፍጹም ፈቃድ ጌታ ወደ መረጠው ስፍራ ቢመጣ፥


ዳዊትም፥ “የቅዒላ ነዋሪዎች እኔንና ሰዎቼን ለሳኦል አሳልፈው ይሰጡናል?” ሲል ጠየቀ። ጌታም፥ “አዎን አሳልፈው ይሰጧችኋል” አለው።


ሳኦል እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ለእኔ ስለ ተቆረቆራችሁ ጌታ ይባርካችሁ፤