La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 12:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱ ግን አምላካቸውን ጌታን ረሱት፤ ስለዚህ ለሓጾር የጦር አዛዥ ለሲሣራ፥ ለፍልስጥኤማውያንና ለሞዓብ ንጉሥ አሳልፎ ሰጣቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እነርሱ ግን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ረሱት፤ ስለዚህ ለአሦር የጦር አዛዥ ለሲሣራ፣ ለፍልስጥኤማውያንና ለሞዓብ ንጉሥ አሳልፎ ሸጣቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን ሕዝቡ አምላካቸውን እግዚአብሔርን ረሱ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሓጾር ሠራዊት አዛዥ ለነበረው ለሲሣራ፥ ለፍልስጥኤማውያን፥ ለሞአብም ንጉሥ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም እስራኤላውያንን ድል ነሡ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረሱ፤ ለአ​ሶር ሠራ​ዊ​ትም አለቃ ለሲ​ሣራ እጅ፥ ለፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ፥ ለሞ​ዓ​ብም ንጉሥ እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ወጉ​አ​ቸው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረሱ፥ ለአሶር ሠራዊትም አለቃ ለሲሣራ እጅ፥ ለፍልስጥኤማውያንም እጅ፥ ለሞዓብም ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ ከእነርሱም ጋር ተዋጉ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 12:9
15 Referencias Cruzadas  

ለሕዝቤ ለእስራኤል መሪዎች ከሾምሁለት ጊዜ አንሥቶ እንዳደረጉበት ከእንግዲህ አያደርጉበትም፤ ከጠላቶችህ ሁሉ አሳርፍሃለሁ። ከዚህም በላይ ጌታ ራሱ ቤት እንደሚሠራልህ ይነግርሃል፤


ታላቅ ነገርንም በግብጽ፥ ድንቅንም በካም ምድር፥ ግሩም ነገርንም በቀይ ባሕር ያደረገውን ያዳናቸውንም እግዚአብሔርን ረሱ።


እነርሱ ግን ዐመፁ ቅዱስ መንፈሱንም አስመረሩ፤ ስለዚህ ጠላታቸው ሆነ፤ እርሱ ራሱ ተዋጋቸው።


በውኑ ኰረዳ ጌጥዋን ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጣጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን በቍጥር ለማይቆጠሩ ቀናቶች ረስተውኛል።


የወለደህን አምላክ ተውህ፥ የፈጠረህን እግዚአብሔር ረሳህ።”


እርሱ አንባቸው ካልሸጣቸው፥ ጌታም አሳልፎ ካልሰጣቸው፥ እንዴት አንዱ ሺህን ያሳድዳል? ሁለቱስ እንዴት ዐሥር ሺህ ያባርራሉ?


የጌታ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ በፍልስጤማውያንና በአሞናውያን እጅም አሳልፎ ሰጣቸው፤


እስራኤላውያን እንደገና በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ስለዚህም ጌታ በፍልስጥኤማውያን እጅ አርባ ዓመት እንዲገዙ አሳልፎ ሰጣቸው።


ስለዚህ ጌታ በእስራኤል ላይ በመቈጣቱ ለሚዘርፏቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ በዙሪያቸው ላሉ ጠላቶቻቸው ሸጣቸው።


እስራኤላውያን እንደገና በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ይህን ክፋት በጌታ ፊት በማድረጋቸው፥ ጌታ የሞዓብ ንጉሥ ዔግሎን በእስራኤል ላይ እንዲበረታባቸው አደረገ።


ከኤሁድ በኋላ ስድስት መቶ ፍልስጥኤማውያንን በበሬ መንጃ የገደለው የዓናት ልጅ ሻምጋር ተነሣ፤ እርሱም እንደዚሁ ደግሞ እስራኤልን አዳነ።


ስለዚህም ጌታ በሐጾር ሆኖ ይገዛ ለነበረው ለከነዓን ንጉሥ ለያቢን አሳልፎ ሰጣቸው። የያቢን ሠራዊት አዛዥ፥ በሐሮሼትሐጎይም የሚኖረው ሲሣራ ነበረ።


ጌታን የማትሰሙና የማትታዘዙ፥ በትእዛዛቱም ላይ የምታምጹ ከሆነ ግን፥ እጁ በአባቶቻችሁ ላይ እንደ ነበረች ሁሉ በእናንተም ላይ ትሆናለች።