“አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ! እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይጥልሃል።
1 ሳሙኤል 12:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤልም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “አትፍሩ፤ ይህን ሁሉ ክፋት አድርጋችኋል፤ ሆኖም ጌታን በፍጹም ልባችሁ አምልኩት እንጂ ጌታን ከመከተል ፈቀቅ አትበሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤልም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “አትፍሩ፤ ይህን ሁሉ ክፋት አድርጋችኋል፤ ሆኖም እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ አምልኩት እንጂ እግዚአብሔርን ከመከተል ፈቀቅ አትበሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “አይዞአችሁ አትፍሩ፤ ይህን የመሰለ ክፉ ነገር ያደረጋችኹ ብትሆኑ እንኳ በሙሉ ልባችሁ እርሱን አገልግሉት እንጂ ፊታችሁን ከእግዚአብሔር ወደ ሌላ አትመልሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ሕዝቡን ሁሉ አላቸው፥ “አትፍሩ፤ በእውነት ይህን ክፋት ሁሉ አደረጋችሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ አምልኩት እንጂ እግዚአብሔርን ከመከተል ፈቀቅ አትበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም ሕዝቡን አለ፦ አትፍሩ፥ በእውነት ይህን ክፋት ሁሉ አደረጋችሁ፥ ነገር ግን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ አምልኩት እንጂ እግዚአብሔርን ከመከተል ፈቀቅ አትበሉ። |
“አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ! እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይጥልሃል።
በማግስቱም ሙሴ ለሕዝቡ “እናንተ ታላቅ ኃጢአት ሠርታችኋል፤ አሁንም ወደ ጌታ እወጣለሁ፤ ምናልባት ኃጢአታችሁን አስተሰርይላችኋለሁ ይሆናል” አላቸው።
እነሆ፦ “ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ ከእርሱም ብትሄድ ሌላም ወንድ ብታገባ፥ በውኑ በድጋሚ ወደ እርሷ ይመለሳልን? ያች ምድር እጅግ የረከሰች አትሆንምን? አንቺ ከብዙ ውሽሞች ጋር አመንዝረሻል፥ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል ጌታ።
“እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ ጌታ አምላክህ ከአንተ የሚፈልገው ምንድነው? ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔርን እንድትፈራው፥ በመንገዱም ሁሉ እንድትሄድ፥ ጌታ አምላክህንም እንድትወደው፥ በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ እንድታመልከው፥
እኔ ከሞትሁ በኋላ ፈጽማችሁ እንደምትረክሱ፥ ካዘዝኋችሁም መንገድ ዘወር እንደምትሉ ዐውቃለሁና። በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ስለምትፈጽሙ፥ እጆቻችሁ በሠሯቸውም ነገሮች እርሱን ስለምታስቆጡት በሚመጡት ዘመናት ጥፋት ይደርስባችኋል።”
ነገር ግን በገርነትና በአክብሮት አድርጉት፤ በክርስቶስ ያላችሁን መልካም ጠባይ በመንቀፍ የሚናገሩ ሰዎች በሐሜታቸው እንዲያፍሩ መልካም ሕሊና ይኑራችሁ።
ሕዝቡም ሁሉ ሳሙኤልን፥ “ሌላው በደላችን ሳያንስ፥ ንጉሥ እንዲነግሥልን በመጠየቃችን ተጨማሪ ክፋት ስላደረግን እንዳንሞት፥ ለአገልጋዮችህ ወደ አምላክህ ወደ ጌታ ጸልይልን” አሉት።