1 ነገሥት 22:44 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ሕዝቡ በእነዚያ ቦታዎች መሥዋዕት ማቅረብና ዕጣን የማጠን ተግባሩን አልተወም ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ኢዮሣፍጥ ከእስራኤል ንጉሥ ጋራ በሰላም ኖረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮሣፍጥም ከእስራኤል ንጉሥ ጋር ሰላም መሥርቶ ይኖር ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮሣፍጥም ከእስራኤል ንጉሥ ጋር ታረቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮሣፍጥም ከእስራኤል ንጉሥ ጋር ታረቀ። |
ሰሎሞን ጌታን ይወድ ነበር፤ የአባቱንም የዳዊትን መመሪያ ይጠብቅ ነበር፤ ይሁን እንጂ እንስሶችን እያረደ በተለያዩ ኰረብቶች ላይ መሥዋዕት ያቀርብ፥ ዕጣንም ያጥን ነበር።
ሚስቱም የአክዓብ ልጅ ስለ ነበረች እንደ አክዓብ ቤተሰብ የእስራኤል ነገሥታት ይፈጽሙት የነበረውን የክፋት መንገድ ተከተለ፤ በደል በመሥራትም እግዚአብሔርን አሳዘነ፤
ባለ ራእዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፥ ንጉሡንም ኢዮሣፍጥን እንዲህ አለው፦ “ከሐዲውን ታግዛለህን? ወይስ ጌታን የሚጠሉትን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከጌታ ዘንድ ቁጣ ሆኖብሃል።
የአክአብንም ልጅ አግብቶ ነበርና የአክዓብ ቤት እንዳደረገው እንዲሁ በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ በጌታም ዘንድ ክፉ የሆነውን ነገር አደረገ።