1 ነገሥት 1:47 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንጉሡም ባርያዎች ገብተው፦ ‘እግዚአብሔር የሰሎሞንን ስም ከስምህ ዙፋኑንም ከዙፋንህ የበለጠ ያድርግ!’ ብለው ጌታችንን ንጉሡን ዳዊትን ባረኩ፥ ንጉሡም በአልጋው ላይ ሆኖ ሰገደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመንግሥቱ ሹማምትም ወደ ጌታችን ወደ ንጉሥ ዳዊት መጥተው፣ ‘አምላክህ የሰሎሞንን ስም ከአንተ ስም የላቀ፣ ዙፋኑንም ከአንተ ዙፋን የበለጠ ያድርገው’ በማለት ባረኩት። ንጉሡም ዐልጋው ላይ ሆኖ በመስገድ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በላይ ከፍተኛ ሥልጣን ያላቸው ባለሟሎች ሁሉ ወደ ንጉሥ ዳዊት ቀርበው ‘አምላክህ እግዚአብሔር ሰሎሞንን ከአንተ ይበልጥ ዝናው የገነነ፥ መንግሥቱንም ይበልጥ ታላቅ ያድርገው!’ ሲሉ አክብሮታቸውን ገልጠዋል፤ ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳዊት በአልጋው ላይ ሳለ ለእግዚአብሔር ሰገደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የንጉሡም አገልጋዮች ገብተው፦ ‘እግዚአብሔር የሰሎሞንን ስም ከስምህ ይልቅ መልካም ያድርግ፤ ዙፋኑንም ከዙፋንህ የበለጠ ያድርግ’ ብለው ጌታቸውን ንጉሡ ዳዊትን መረቁ፤” ንጉሡም በአልጋው ላይ ሆኖ ሰገደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የንጉሡም ባሪያዎች ገብተው ‘እግዚአብሔር የሰሎሞንን ስም ከስምህ ዙፋኑንም ከዙፋንህ የበለጠ ያድርግ!’ ብለው ጌታችንን ንጉሡን ዳዊትን ባረኩ፤ ንጉሡም በአልጋው ላይ ሆኖ ሰገደ። |
ቶዒ ከሀዳድዔዜር ጋር ሁልጊዜ ይዋጋ ስለ ነበር፥ ልጁን ዮራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ለሰላምታና በሀዳድዔዜር ላይ ሰለተቀዳጀውም ድል ደስታውን እንዲያቀርብለት ላከው፤ ልጁም የብር፥ የወርቅና የናስ ዕቃ ይዞ መጣ።