1 ነገሥት 1:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬዎችንና ፍሪዳዎችን በጎችንም ሠውቶአል፥ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ የሠራዊቱንም አለቃ ኢዮአብን። ካህኑንም አብያታርን ጠርቶአል፥ እነሆም፥ በፊቱ እየበሉና እየጠጡ፦ ‘አዶንያስ ሺህ ዓመት ይንገሥ’ ይላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዛሬው ቀን ታች ወርዶ ብዙ በሬዎች፣ ኰርማዎችና በጎች ሠውቷል፤ የንጉሡን ልጆች በሙሉ፣ የሰራዊቱን አዛዦችና ካህኑን አብያታርንም ጠርቷል። እነሆ፤ አሁን፣ ‘አዶንያስ ለዘላለም ይኑር’ እያሉ ከርሱ ጋራ በመብላትና በመጠጣት ላይ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዶንያስ በዛሬው ዕለት ብዙ ጥጆችንና የሰቡ ኰርማዎችን፥ በጎችን ዐርዶ መሥዋዕት አቅርቦአል፤ ሌሎቹን የንጉሡን ልጆች የሠራዊትህን አዛዥ ኢዮአብንና ካህኑን አብያታርን ጋብዞአል፤ እነሆ አሁን በዚህ ሰዓት “ረጅም ዕድሜ ለንጉሥ አዶንያስ!” በማለት እየደነፉ ከእርሱ ጋር በመብላትና በመጠጣት ላይ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬዎችንና ጠቦቶችን፥ በጎችንም ሠውቶአል፤ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ የሠራዊቱን አለቃ ኢዮአብን፥ ካህኑንም አብያታርን ጠርቶአል፤ እነሆም፥ በፊቱ እየበሉና እየጠጡ፦ አዶንያስ ሺህ ዓመት ይንገሥ ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬዎችንና ፍሪዳዎችን በጎችንም ሠውቶአል፤ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ የሠራዊትንም አለቃ ኢዮአብን፥ ካህኑንም አብያታርን ጠርቶአል፤ እነሆም፥ በፊቱ እየበሉና እየጠጡ ‘አዶንያስ ሺህ ዓመት ይንገሥ!’ ይላሉ። |
እርሱም ብዙ በሬዎችንና ፍሪዳዎችን በጎችንም ሠውቶአል፥ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ ካህኑንም አብያታርን፥ የሠራዊቱንም አለቃ ኢዮአብን ጠርቶአል፥ ባርያህን ስሎሞንን ግን አልጠራውም።
በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርገው ይቀቡት፥ ቀንደ መለከትም ነፍታችሁ፥ ‘ሰሎሞን ሺህ ዓመት ይንገሥ’ በሉ።
አዶንያስም በጎችንና በሬዎችን ፍሪዳዎችንም በዔንሮጌል አጠገብ ባለችው በዞሔሌት ድንጋይጋ ሠዋ፥ የንጉሡንም ልጆች ወንድሞቹን ሁሉ፥ የንጉሡንም ባርያዎች፥ የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ጠራ።
አዶንያስም እንዲህ አላት፦ “ንጉሥ መሆን የሚገባኝ እኔ እንደ ነበርኩና ይህንንም በእስራኤል ምድር የሚኖር ሁሉ በተስፋ ይጠባበቅ እንደ ነበር አንቺ ራስሽ ታውቂያለሽ፤ ነገር ግን ጉዳዩ ከጌታ ስለ ተወሰነ ለእኔ መሰጠት የሚገባው መንግሥት ተላልፎ ለወንድሜ ሆኖአል።
ከዚያም በኋላ ዮዳሄ ኢዮአስን አውጥቶ በራሱ ላይ ዘውድ ጫነበት፤ ለመንግሥቱ መመሪያ የሆነውንም ሕግ አንድ ቅጂ አስረከበው፤ በዚህ ዓይነት ኢዮአስ ተቀብቶ ነገሠ፤ ሕዝቡም እያጨበጨበ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ!” አለ።
እዚያም እንደ ደረሰች አዲሱ ንጉሥ በተለመደው ባህል መሠረት በቤተ መቅደሱ መግቢያ በሚገኘው ዐምድ አጠገብ ቆሞ አየችው፤ እርሱም በጦር አዛዦችና በእምቢልታ ነፊዎች ታጅቦ ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ በደስታ ተሞልተው እልል እያሉ እምቢልታ ይነፉ ነበር፤ ዐታልያም በድንጋጤ ልብስዋን ቀዳ “ይህ በክሕደት የተፈጸመ ሤራ ነው! ሤራ ነው!” ስትል ጮኸች።
ወዲያውኑ የኢዩ ጓደኞች የነበሩት የጦር መኰንኖች ልብሳቸውን እያወለቁ ኢዩ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፤ በዚያም ላይ እንዲቆም አድርገው እምቢልታ ነፉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ኢዩ ነግሦአል!” ሲሉ ጮኹ።
በማግስቱም ለጌታ መሥዋዕት ሰዉ፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ለጌታ አቀረቡ፤ አንድ ሺህ ወይፈን፥ አንድ ሺህም አውራ በጎች፥ አንድ ሺህም የበግ ጠቦቶች፥ የመጠጥ ቁርባናቸውንም፥ ስለ እስራኤልም ሁሉ ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ።
ከፊቱ ይሄዱ የነበሩትና ይከተሉት የነበሩት ሕዝብ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሣዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር።
ሌሎች ባርያዎችን ደግሞ ልኮ ‘የታደሙትን እነሆ ድግሴን አዘጋጅቻለሁ፤ ሰንጋዎቼና የሰቡት ከብቶቼ ታርደዋል፤ ሁሉም ተዘጋጅቶአል፤ ወደ ሰርጉ ግብዣ ኑ፤ በሉአቸው፤’ አለ።
ሳሙኤልም መላውን ሕዝብ፥ “ጌታ የመረጠውን ሰው አያችሁን? ከሕዝቡ ሁሉ የሚስተካከለው ማንም የለም” አለ። ከዚያም ሕዝቡ፥ “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ ይሁን!” ብሎ ጮኸ።