1 ዮሐንስ 5:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምስክርነቱ ይህ ነው፦ እግዚአብሔር የዘለዓለምን ሕይወት ሰጠን፥ ይህም ሕይወት ያለው በልጁ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምስክርነቱም ይህ ነው፤ እግዚአብሔር የዘላለምን ሕይወት ሰጠን፤ ይህም ሕይወት ያለው በልጁ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምስክርነቱም እግዚአብሔር የዘለዓለም ሕይወት እንደ ሰጠንና ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ የሚመሰክር ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። |
ይህም የሆነው፥ ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ፥ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለዘለዓለም ሕይወት፥ በጽድቅ በኩል እንዲነግሥ ነው።
ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ ዋነኛ በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ በማሳየት፥ በእርሱ አምነው የዘለዓለም ሕይወትን ለሚያገኙ ምሳሌ እንድሆን አደረገኝ፥ በእዚህም ምክንያት ምሕረትን አገኘሁ።
ፍቅር በዚህ ነው፥ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን ነገር ግን እርሱ እንደ ወደደን እና ለኃጢአታችንም ማስተስሪያ እንዲሆን ልጁን ስለላከልን ነው።
በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በራሱ ምስክር አለው፤ እግዚአብሔርን የማያምን ግን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክርነት ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።
የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣ፥ እውነት የሆነውን እንድናውቅ ማስተዋልን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነት በሆነው በእርሱ እንኖራለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።
ድሜጥሮስ በሁሉም ተመስክሮለታል፤ እውነት ራስዋም ትመሰክርለታለች፤ እኛም እንመሰክርለታለን፤ ምስክርነታችን ደግሞ እውነት እንደሆነ ታውቃለህ።