1 ቆሮንቶስ 9:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይስ ሥራን ለመተው መብት የሌለን እኔና በርናባስ ብቻ ነን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይስ ያለመሥራት መብት የሌለን እኔና በርናባስ ብቻ ነን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወይስ በሥራ እየጣርን መኖር የሚገባን በርናባስና እኔ ብቻ ነንን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይስ ሥራን ለመተው መብት የሌለን እኔና በርናባስ ብቻ ነን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይስ ሥራን ለመተው መብት የሌለን እኔና በርናባስ ብቻ ነን? |
በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት፥ በአምላካችን ቤት ወደ ሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥
አይሁድ ግን የሚያመልኩትን የከበሩትንም ሴቶችና የከተማውን መኳንንት አወኩ፤ በጳውሎስና በበርናባስም ላይ ስደትን አስነሥተው ከአገራቸው አወጡአቸው።
ወንድሞች ሆይ! ድካማችንንና ጥረታችንን ታስታውሱታላችሁ፤ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እየሰበክን በአንዳችሁም ላይ እንኳ ሸክም ላለመሆን ስንል ሌሊትና ቀን እንሠራ ነበር።