1 ቆሮንቶስ 15:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን የሆንሁትን ሆኛለሁ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋ ከንቱ አልሆነም፤ ይልቁን ከሁሉም በላይ በትጋት ሠርቻለሁ፤ ሆኖም ግን እኔ ሳልሆን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን የሆንሁትን ሆኛለሁ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋ ከንቱ አልሆነም፤ እንዲያውም ከሁሉም በላይ በትጋት ሠርቻለሁ፤ ዳሩ ግን እኔ ሳልሆን ከእኔ ጋራ ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እኔ አሁን የሆንኩትን ሆኜ የምገኘው በእግዚአብሔር ጸጋ ነው፤ የተሰጠኝም ጸጋ ያለ ፍሬ አልቀረም፤ እንዲያውም ከሌሎቹ ይበልጥ በሥራ ደክሜአለሁ፤ ነገር ግን ይህን ያደረገው ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን እኔ ባለሁበት አለሁ፤ ለእኔም የሰጠኝ ጸጋው ለከንቱ የሆነብኝ አይደለም፤ እኔም ከሁሉ ይልቅ ደከምሁ፤ ነገር ግን በእኔ ላይ ያደረው የእግዚአብሔር ጸጋ አጸናኝ እንጂ እኔ አይደለሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም ከሁላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ፥ ዳሩ ግን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም። |
እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችሁ እንደሰጣችሁ እምነት መጠን፥ በረጋ አእምሮ አስቡ እንጂ ማሰብ ከሚገባችሁ በላይ ራሳችሁን ከፍ አድርጋችሁ እንዳታስቡ በተሰጠኝ ጸጋ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ እናገራለሁና።
የእግዚአብሔር ጸጋ እንደተሰጠኝ መጠን እንደ ብልኅ ግንበኛ መሠረትን ጣልኩ፤ ሌላውም በዚያ ላይ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በዚያ ላይ እንዴት እንደሚያንጽ ይጠንቀቅ።
አንተን እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልከውስ ምን አለህ? እንግዲህ የተቀበልክ ከሆንክ፥ እንዳልተቀበልክ የምትመካው ስለ ምንድነው?
በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ! ይህ እናንተ ግድ ስላላችሁኝ የሆነ ነው። እኔ ከምንም የማልቆጠር ብሆን እንኳን፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አላንስምና፥ በእርግጥም እናንተ ስለ እኔ መናገር ይገባችሁ ነበር።