1 ቆሮንቶስ 11:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አመሰገነ ቆርሶም “እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት፤” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከባረከ በኋላ ቈርሶ፣ “ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ለመታሰቢያዬም አድርጉት” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምስጋናም ጸሎት አድርጎ ቈረሰውና “[እንካችሁ ብሉ፤] ይህ ለእናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አመሰገነ፤ ባረከ፤ ፈተተ፤ እንዲህም አላቸው፥ “እንኩ ብሉ፤ ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ መታሰቢያዬንም እንዲሁ አድርጉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት በዚያች ሌሊት እንጀራን አንሥቶ አመሰገነ፥ ቆርሶም፦ እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ። |
የእስራኤል ልጆች የመታሰቢያ ድንጋዮች እንዲሆኑ ሁለቱን ዕንቁዎች በኤፉዱ ትከሻዎች ላይ ታደርጋለህ፤ አሮንም በሁለቱ ትከሻዎቹ ላይ ለመታሰቢያ እንዲሆን ስማቸውን በጌታ ፊት ይሸከማል።
ሳበኝ፥ ከአንተም በኋላ እንሮጣለን፥ ንጉሥ ወደ ቤቱ አገባኝ፥ በአንተ ደስ ይለናል፥ ሐሤትም እናደርጋለን፥ ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅርህን እናስባለን፥ በቅንነት ይወድዱሃል።
እኅቴ ሙሽራዬ ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከርቤዬን ከቅመሜ ጋር ለቀምሁ፥ እንጀራዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወይን ጠጄን ከወተቴ ጋር ጠጣሁ። ባልንጀሮቼ ሆይ፥ ብሉ፥ ጠጡ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ እስክትረኩ ድረስ ጠጡ።
የሠራዊት ጌታም ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፥ ያረጀ የወይን ጠጅ፥ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፥ መልካምና የበሰለ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል።
እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ “ይህ ጽዋ በደሜ የሚመሰረት አዲስ ኪዳን ነው፤ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት፤” አለ።
እናንተ እንዲህ ትሉአቸዋላችሁ፦ በጌታ ቃል ኪዳን ታቦት ፊት የዮርዳኖስ ውኃ ስለተቋረጠ ነው፤ ዮርዳኖስን በተሻገረ ጊዜ የዮርዳኖስ ውኃ ተቋረጠ፥ እነዚህም ድንጋዮች ለእስራኤል ልጆች ለዘለዓለም መታሰቢያ የሆኑ ናቸው።”