Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 11:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 አመ​ሰ​ገነ፤ ባረከ፤ ፈተተ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እንኩ ብሉ፤ ስለ እና​ንተ የሚ​ሰ​ጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ዬ​ንም እን​ዲሁ አድ​ርጉ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ከባረከ በኋላ ቈርሶ፣ “ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ለመታሰቢያዬም አድርጉት” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 አመሰገነ ቆርሶም “እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት፤” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 የምስጋናም ጸሎት አድርጎ ቈረሰውና “[እንካችሁ ብሉ፤] ይህ ለእናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት በዚያች ሌሊት እንጀራን አንሥቶ አመሰገነ፥ ቆርሶም፦ እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 11:24
20 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገድ የቀና ነው፤ በቅ​ዱስ ስሙም ታመን፤ ነፍ​ሳ​ችን የተ​መ​ኘ​ች​ው​ንም አገ​ኘን።


እኅቴ ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከር​ቤ​ዬን ከሽ​ቱዬ ጋር ለቀ​ምሁ፥ እን​ጀ​ራ​ዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወ​ይን ጠጄን ከወ​ተቴ ጋር ጠጣሁ። ባል​ን​ጀ​ሮች በሉ፥ ጠገ​ቡም፤ የወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ጠጡ፥ ሰከ​ሩም፥ ልባ​ቸው የጠፋ ነውና።


“ኑ፥ እንጀራዬን ብሉ፥ የጠመቅሁላችሁን የወይን ጠጅም ጠጡ።


ይህም ቀን መታ​ሰ​ቢያ ይሁ​ና​ችሁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዓል ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም ሥር​ዐት ሆኖ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሕ​ዝቡ ሁሉ ግብ​ዣን ያደ​ር​ጋል፤ በዚህ ተራራ ላይ ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋሉ፤ የወ​ይን ጠጅ​ንም ይጠ​ጣሉ፤ ዘይ​ት​ንም ይቀ​ባሉ።


ከወደ ኋላ​ህም ሳቡህ፥ በሽ​ቱህ መዓ​ዛም እን​ሮ​ጣ​ለን፤ ንጉሡ ወደ እል​ፍኙ አገ​ባኝ፤ በአ​ንቺ ደስ ይለ​ኛል፥ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ ከወ​ይን ጠጅ ይልቅ ጡቶ​ች​ሽን እን​ወ​ዳ​ለን፤ አን​ቺ​ንም መው​ደድ የተ​ገባ ነው።


ለቅ​ኖች ብር​ሃን በጨ​ለማ ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነው፤ አም​ላ​ካ​ች​ንም ጻድቅ ነው።


እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል።”


አንተ በም​ድር ሁሉ ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ስን​ሻ​ገር የዮ​ር​ዳ​ኖስ ወንዝ ስለ ደረቀ ነው፤ እነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮ​ችም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለዘ​ለ​ዓ​ለም መታ​ሰ​ቢያ ይሆ​ናሉ።”


ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም የመ​ታ​ሰ​ቢያ ድን​ጋ​ዮች ይሆኑ ዘንድ ሁለ​ቱን ዕን​ቍ​ዎች በል​ብሰ መት​ከፉ ጫን​ቃ​ዎች ላይ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ አሮ​ንም በሁ​ለቱ ጫን​ቃ​ዎች ላይ ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ስማ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይሸ​ከ​ማል።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተማ​ርሁ አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እር​ሱን ራሱን በያ​ዙ​ባት በዚ​ያች ሌሊት ኅብ​ስ​ቱን አነሣ።


እን​ዲ​ሁም ኅብ​ስ​ቱን ከተ​ቀ​በሉ በኋላ ጽዋ​ውን አን​ሥቶ፥ “አዲስ ሥር​ዐት የሚ​ጸ​ና​በት ይህ ጽዋ ደሜ ነው እን​ዲህ አድ​ርጉ፤ በም​ት​ጠ​ጡ​በ​ትም ጊዜ አስ​ቡኝ” አላ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios