1 ዜና መዋዕል 5:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፎሐን መንፈስ፥ የአሦርንም ንጉሥ የቴልጌል-ቴልፌልሶርን መንፈስ አስነሣ፤ የሮቤልንና የጋድን ልጆች የምናሴንም ነገድ እኩሌታ አፈለሰ፥ እስከ ዛሬም ወዳሉበት ወደ አላሔና ወደ አቦር፥ ወደ ሃራና ወደ ጎዛን ወንዝ አመጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፎሓን መንፈስ ይኸውም የቴልጌልቴልፌልሶርን መንፈስ አነሣሥቶ የሮቤልን፣ የጋድንና፣ የምናሴን ነገድ እኩሌታ ማርኮ እንዲወስድ አደረገ። እነዚህንም ወደ አላሔ፣ ወደ አቦር፣ ወደ ሃራና ወደ ጎዛን ወንዝ ዳርቻ አፈለሳቸው፤ እነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይገኛሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እግዚአብሔር ፑል ወይም ቲግላት ፐሌሴር ተብሎ የሚጠራውን የአሦርን ንጉሠ ነገሥት አነሣሥቶ ምድራቸውን እንዲወር አደረገ፤ በዚህ ዐይነት ቲግላት ፐሌሴር የሮቤልን፥ የጋድንና በምሥራቅ በኩል ያለውን የምናሴን ነገድ እኩሌታ ማርኮ በመውሰድ በሐላሕ፥ በሐቦርና በሃራ እንዲሁም በጎዛን ወንዝ ዳርቻ እንዲኖሩ አደረጋቸው እስከ ዛሬም ድረስ በዚያው ይገኛሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፋሎክን መንፈስ፥ የአሦርንም ንጉሥ የቴልጌልቴልፌልሶርን መንፈስ አስነሣ፤ የሮቤልንና የጋድን ልጆች የምናሴንም ነገድ እኩሌታ አፈለሰ፥ እስከ ዛሬም ወዳሉበት ወደ አላሔና ወደ ኦቦር፥ ወደ ሃራንና ወደ ጎዛን ወንዝ አመጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፎሐን መንፈስ፥ የአሦርንም ንጉሥ የቴልጌልቴልፌልሶርን መንፈስ አስነሣ፤ የሮቤልንና የጋድን ልጆች የምናሴንም ነገድ እኵሌታ አፈለሰ፤ እስከ ዛሬም ወዳሉበት ወደ አላሔና ወደ አቦር፥ ወደ ሃራና ወደ ጎዛን ወንዝ አመጣቸው። |
የአሦር ንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር እስራኤልን ወረረ፤ ምናሔም በአገሩ መንግሥት ላይ ሥልጣኑን እንዲያጸናለትና እንዲደግፈው ለመማጠን ሠላሳ አራት ሺህ ኪሎ የሚመዝን ብር እጅ መንሻ አድርጎ ለቲግላት ፐሌሴር ሰጠው።
የአሦር ንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር ዒዮን፥ አቤልቤትማዕካ፥ ያኖሐ፥ ቄዴሽና ሐጾር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች፥ እንዲሁም የገለዓድን፥ የገሊላንና የንፍታሌምን ግዛቶች በመውረር ሕዝቡን ወደ አሦር ማርኮ የወሰደውም ይኸው ፋቁሔ በነገሠበት ዘመን ነበር።
ከዚህም የተነሣ ንጉሥ አካዝ ወደ አሦር ንጉሠ ነገሥት ወደ ቲግላት ፐሌሴር “እኔ ለአንተ ታማኝ አገልጋይህ ነኝ፤ ስለዚህም ወደ እኔ መጥተህ አደጋ ከጣሉብኝ ከሶርያና ከእስራኤል ነገሥታት እጅ አድነኝ” የሚል ጥያቄ የያዙ መልእክተኞች ላከ።
ይኸውም ሆሴዕ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ሰልምናሶር ድል አድርጎ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤላውያንንም ማርኮ በእስረኛነት ወደ አሦር ወሰዳቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹ በሐላሕ ከተማ፥ ጥቂቶቹ በጎዛን አውራጃ ውስጥ በሚገኘው በሐቦር ወንዝ አጠገብ፥ እንዲሁም ሌሎቹ በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።
የአሦር ንጉሠ ነገሥት እስራኤላውያንን ማርኮ ወደ አሦር በመውሰድ ከእነርሱ ጥቂቶቹ በሐላሕ ከተማ ጥቂቶቹ በጎዛን አውራጃ በሚገኘው በሐቦር ወንዝ አጠገብ፥ ሌሎቹ ደግሞ በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።
የቀድሞ አባቶቼ የጎዛንን፥ የካራንና የሬጼፍን ከተሞች አጥፍተዋል፤ በተላሳር የሚኖሩትን የዔዳንን ሕዝብ ገድለዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ከአማልክታቸው አንድ እንኳ ሊያድናቸው ችሎአልን?
እንደ ንጉሡም ትእዛዝ መልክተኞቹ እንዲህ የሚለውን የንጉሡንና የሹማምንቱን ደብዳቤ ይዘው ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ሄዱ እንዲህም አሉ፦ “የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታ ከአሦር ነገሥታት እጅ ወዳመለጠ የእናንተ ወደ ሆኑት ትሩፋን እንዲመለስ ወደ አብርሃምና ወደ ይስሐቅ ወደ እስራኤልም አምላክ ተመለሱ።
እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣው የይሁዳና የብንያም የአባቶች አለቆች፥ ካህናቱና ሌዋውያኑም ሁሉ ለመሄድና በኢየሩሳሌም ያለውን የጌታን ቤት ለመሥራት ተዘጋጁ።