1 ዜና መዋዕል 4:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህም የኤጣም አባት ልጆች ናቸው፤ ኢይዝራኤል፥ ይሽማ፥ ይድባሽ፥ እኅታቸውም ሃጽሌልፎኒ ትበባል ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኤጣም ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ኢይዝራኤል፣ ይሽማ፣ ይደባሽ። እኅታቸው ሃጽሌልፎኒ ትባላለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሑር የካሌብና የኤፍራታ በኲር ልጅ ነው፤ ከእርሱ ልጆች መካከል በቤተልሔም የሰፈሩ አሉ፤ ሌሎቹም የሑር ልጆች ጰኑኤልና ዔዜር ናቸው፤ የኤታም ወንዶች ልጆች ኤይዝርኤል፥ ኢሻማ፥ ኤድባሽ፥ ጌዶርን የመሠረተው ፋኑኤልና ሑሻን የመሠረተው ኤጼር ሲሆኑ ሐጽሌልጶኒ የምትባል እኅት ነበረቻቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህም የኤጣም ልጆች ናቸው፤ ኢይዝራኤል፥ ይሰማ፥ ኤጋቢስ፥ እኅታቸውም ኤሴልፎን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህም የኤጣም አባት ልጆች ናቸው፤ ኢይዝራኤል፥ ይሽማ፥ ይድባሽ፥ እኅታቸውም ሃጽሌልፎኒ። |
ከዚያም ሦስት ሺህ ሰዎች ከይሁዳ ተነሥተው በኤታም ዐለት ወዳለው ዋሻ ወርደው ሳምሶንን፥ “ፍልስጥኤማውያን ገዦቻችን መሆናቸውን አታውቅምን? ያደረግህብንስ ነገር ምንድነው?” ብለው ጠየቁት። ሳምሶንም፥ “ያደረግሁት እነርሱ ያደረ ጉብኝን ነው” በማለት መለሰላቸው።