Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 15:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከዚያም ሦስት ሺህ ሰዎች ከይሁዳ ተነሥተው በኤታም ዐለት ወዳለው ዋሻ ወርደው ሳምሶንን፥ “ፍልስጥኤማውያን ገዦቻችን መሆናቸውን አታውቅምን? ያደረግህብንስ ነገር ምንድነው?” ብለው ጠየቁት። ሳምሶንም፥ “ያደረግሁት እነርሱ ያደረ ጉብኝን ነው” በማለት መለሰላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከዚያም ሦስት ሺሕ ሰዎች ከይሁዳ ተነሥተው በኤጣም ዐለት ወዳለው ዋሻ ወርደው ሳምሶንን፣ “ፍልስጥኤማውያን ገዦቻችን መሆናቸውን አታውቅምን? ያደረግህብንስ ነገር ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት። ሳምሶንም፣ “ያደረግሁት እነርሱ ያደረጉብኝን ነው” በማለት መለሰላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ስለዚህም ሦስት ሺህ የሚሆኑ የይሁዳ ሰዎች በዔጣም ወዳለው ዋሻ ሄደው “ፍልስጥኤማውያን ገዢዎቻችን እንደ ሆኑ አታውቅምን? ታዲያ ይህ ያደረግህብን ምንድን ነው?” ሲሉ ሶምሶንን ጠየቁት። እርሱም “እኔ በእነርሱ ላይ ያደረግኹት ልክ እነርሱ በእኔ ላይ ያደረጉትን ነው” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ከይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሦስት ሺህ የሚ​ያ​ህሉ በኢ​ጣም ዓለት ወዳ​ለው ዋሻ ወር​ደው ሶም​ሶ​ንን፥ “ገዢ​ዎ​ቻ​ችን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እን​ደ​ሆኑ አታ​ው​ቅ​ምን? ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ይህ ምን​ድን ነው?” አሉት። ሶም​ሶ​ንም፥ “እን​ዳ​ደ​ረ​ጉ​ባ​ችሁ እን​ዲሁ አደ​ረ​ግ​ሁ​ባ​ቸው” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ከይሁዳም ሰዎች ሦስት ሺህ የሚያህሉ በኤጣም ዓለት ወዳለው ዋሻ ወርደው ሶምሶንን፦ ገዦቻችን ፍልስጥኤማውያን እንደ ሆኑ አታውቅምን? ያደረግህብን ይህ ምንድር ነው? አሉት። እርሱም፦ እንዳደረጉብኝ እንዲሁ አደረግሁባቸው አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 15:11
10 Referencias Cruzadas  

በዚያን ጊዜ በእስራኤል ላይ ገዦቹ ፍልስጥኤማውያን ስለ ነበሩ፥ ከፍልስጥአማውያን ጋር ጠብ እንዲፈጠር ጌታ ሆን ብሎ ያደረገው ነገር መሆኑን አባቱና እናቱ አላወቁም ነበር።


እስራኤላውያን እንደገና በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ስለዚህም ጌታ በፍልስጥኤማውያን እጅ አርባ ዓመት እንዲገዙ አሳልፎ ሰጣቸው።


ጌታም ራስ እንጂ ጅራት አያደርግህም። ዛሬ የምሰጥህን የጌታ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብትታዘዝ በጥንቃቄም ብትጠብቅ ሁልጊዜም በላይ እንጂ እታች አትሆንም።


የቃል ኪዳኑንም በቀል የሚበቀል ሰይፍ አመጣባችኋለሁ፤ ወደ ከተሞቻችሁም ትሰበሰባላችሁ፥ በመካከላችሁም ቸነፈርን እልክባችኋለሁ፤ በጠላትም እጅ ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ።


“በመካከልህ የሚኖር መጻተኛ ከአንተ በላይ ከፍ ከፍ ሲል አንተ ግን ዝቅ ዝቅ ትላለህ።


የይሁዳም ሰዎች፥ “ልትወጉን የመጣችሁት ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቋቸው። እነርሱም “እኛ የመጣነው ሳምሶንን ልና ስርና ያደረገብንን ልናደርግበት ነው” ብለው መለሱላቸው።


እነርሱም፥ “አስረን ለፍልስጥአማውያን ልንሰጥህ ይኸው መጥተናል” አሉት። ሳምሶንም፥ “እናንተ ራሳችሁ ላትገድሉኝ ማሉልኝ” አላቸው።


እነዚህም የኤጣም አባት ልጆች ናቸው፤ ኢይዝራኤል፥ ይሽማ፥ ይድባሽ፥ እኅታቸውም ሃጽሌልፎኒ ትበባል ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios