ከዚያም በኋላ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ መርከበኞቹ ከኢዮሣፍጥ መርከበኞች ጋር በኅብረት እንዲሠሩ የውል ድርድር አቅርቦ ነበር፤ ኢዮሣፍጥ ግን ሐሳቡን አልተቀበለም።
1 ዜና መዋዕል 3:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጁ ኢዮራም፥ ልጁ አካዝያስ፥ ልጁ ኢዮአስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም፣ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣ የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮራም፥ አካዝያስ፥ ኢዮአስ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጁ ኢዮራም፥ ልጁ አካዝያስ፥ ልጁ ኢዮአስ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጁ ኢዮራም፥ ልጁ አካዝያስ፥ ልጁ ኢዮአስ፥ |
ከዚያም በኋላ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ መርከበኞቹ ከኢዮሣፍጥ መርከበኞች ጋር በኅብረት እንዲሠሩ የውል ድርድር አቅርቦ ነበር፤ ኢዮሣፍጥ ግን ሐሳቡን አልተቀበለም።
ከእርሷም እጅ ማምለጥ የቻለ የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ ብቻ ነበር፤ እርሱም እንኳ ከሌሎቹ ጋር እንዲገደል ተመክሮበት ነበር፤ ነገር ግን አክስቱ የነበረችው በአባትዋ በኩል የንጉሥ አካዝያስ እኅት የሆነችው፥ የንጉሥ ኢዮራም ልጅ ይሆሼባዕ በመደበቅ ከሞት አዳነችው፤ እርሷም እርሱንና ሞግዚቱን ወስዳ በቤተ መቅደሱ ግቢ በሚገኘው ማረፊያ ክፍል ውስጥ ስለ ደበቀችው በዐታልያ እጅ ሳይገደል ቀረ።
ኢዩ በእስራኤል በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ኢዮአስ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ አርባ ዓመት ገዛ፤ የእርሱ እናት ጺቢያ ተብላ የምትጠራ የቤርሳቤህ ከተማ ተወላጅ ነበረች።
ወደ ይሁዳም ወጡ፥ ወረርዋትም፥ የንጉሡንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ወንዶች ልጆቹንም ሴቶች ልጆቹንም ማረኩ፤ ከታናሹም ልጅ ከአካዝያስ በቀር ልጅ አላስቀሩለትም።
ከሶርያም ንጉሥ ከአዛኤል ጋር በተዋጋ ጊዜ ሶርያውያን በሬማት ያቈሰሉትን ቁስል ለመታከም ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ፤ ታምሞም ነበርና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የአክዓብን ልጅ ኢዮራምን ለማየት ወደ ኢይዝራኤል ወረደ።
ኢዮአስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሰባት ዓመት ልጅ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም አርባ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ሳብያ የተባለች የቤርሳቤህ ሴት ነበረች።