1 ዜና መዋዕል 27:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአኪጦፌልም ቀጥሎ የበናያስ ልጅ ዮዳሄና አብያታር ነበሩ፤ ኢዮአብም የንጉሡ ሠራዊት አለቃ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የበናያስ ልጅ ዮዳሄና አብያታር በአኪጦፌል እግር ተተኩ። ኢዮአብም የንጉሡ የክብር ዘብ አዛዥ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አኪጦፌል ከሞተ በኋላም አብያታርና የበናያ ልጅ ይሆያዳዕ የንጉሡ አማካሪዎች ሆኑ፤ ኢዮአብ ደግሞ የንጉሡ ሠራዊት አዛዥ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአኪጦፌልም ቀጥሎ የበናያስ ልጅ ዮዳሔና አብያታር ነበሩ፤ ኢዮአብም የንጉሡ ሠራዊት አለቃ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአኪጦፌልም ቀጥሎ የበናያስ ልጅ ዮዳሄና አብያታር ነበሩ፤ ኢዮአብያም የንጉሡ ሠራዊት አለቃ ነበረ። |