Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 27:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 አኪጦፌልም የንጉሡ አማካሪ ነበረ፤ አርካዊውም ኩሲ የንጉሡ ወዳጅ ነበረ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 አኪጦፌል የንጉሡ አማካሪ ሲሆን፣ አርካዊው ኩሲ ደግሞ የንጉሡ ወዳጅ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 አኪጦፌል የንጉሡ አማካሪ ሲሆን፥ አርካዊው ሑሻይ የንጉሡ ወዳጅ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 አኪ​ጦ​ፌ​ልም የን​ጉሡ አማ​ካሪ ነበረ። አር​ካ​ዊው ኩሲም የን​ጉሡ አን​ደኛ ወዳጅ ነበረ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 አኪጦፌልም የንጉሡ አማካሪ ነበረ፤ አርካዊውም ኩሲ የንጉሡ ወዳጅ ነበረ፤

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 27:33
10 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ የዳዊት ወዳጅ ሑሻይ ልክ አቤሴሎም ኢየሩሳሌም በገባበት ሰዓት ወደ ከተማዋ ደረሰ።


አቤሴሎም መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ የሆነው ጊሎአዊው አኪጦፌል ከአገሩ ከጊሎ ወደ እርሱ እንዲመጣ ላከበት፤ ስለዚህ ሤራው ጥንካሬ አገኘ፤ የአቤሴሎምም ተከታዮች ቍጥር እየበዛ ሄደ።


ዳዊት ሕዝቡ እግዚአብሔርን ወደሚያመልክበት ወደ ተራራው ጫፍ በደረሰ ጊዜ፥ አርካዊው ሑሻይ ልብሱን ቀዶ ትቢያ በራሱ ላይ ነስንሶ ሊያገኘው መጣ።


ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ በጎቹም እንዲበተኑ እረኛውን ምታ፤ እጄንም በታናናሾች ላይ አዞራለሁ።


ጠላትስ ቢሰድበኝ፥ በታገሥሁ ነበር፥ የሚጠላኝም ራሱን በላዬ ከፍ ከፍ ቢያደርግ፥ ከእርሱ በተሸሸግሁ ነበር።


አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተከተሉት ባየ ጊዜ፥ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወደሚገኝበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም አስተካክሎ በገዛ እጁ ታነቀ፤ ከሞተ በኋላ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።


በዚያም ጊዜ አኪጦፌል የሚሰጠው ምክር ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ መጠየቅ ይቆጠር ነበር፤ በዳዊትም ሆነ በአቤሴሎም የአኪጦፌል ምክር ይከበር ነበር።


አስተዋይና ጸሐፊ የነበረው የዳዊት አጎት ዮናታን አማካሪ ነበረ፤ የሐክሞኒም ልጅ ይሒኤል የንጉሡን ልጆች ያገለግል ነበረ፤


ዓዛርያስ የተባለው የናታን ልጅ፦ የክፍላተ ሀገር ገዢዎች የበላይ ኀላፊ፤ የናታን ልጅ ካህኑ ዛቡድ፦ የንጉሡ አማካሪና ወዳጅ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios