1 ዜና መዋዕል 26:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኬብሮናውያን ሐሸብያና ወንድሞቹ፥ ጽኑዓን የነበሩት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች፥ ለጌታ ሥራ ሁሉ ለንጉሡም አገልግሎት በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል ባለው በእስራኤል ላይ ተሾመው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኬብሮናውያን፤ ለሐሻብያ፣ ጠንካራና ጐበዝ የሆኑ አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ሰዎች ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ በሚገኘው የእስራኤል ምድር ላለው የእግዚአብሔር ሥራና ለንጉሡም አገልግሎት ኀላፊዎች ሆነው ተመደቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኬብሮናውያን ወገን ሐሻብያና ወንድሞቹ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ከዮርዳኖስ በስተምዕራብ ባለው በእስራኤል አገር ለመንፈሳዊ ሥራና ለመንግሥት አገልግሎት ኀላፊዎች ሆነው ተመደቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኬብሮናውያን ሐሳብያና ወንድሞቹ፥ ጽኑዓን የነበሩት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች፥ ለእግዚአብሔር ሥራ ሁሉ፥ ለንጉሡም አገልግሎት በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል ባለው በእስራኤል ላይ ተሾመው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኬብሮናውያን ሐሸብያና ወንድሞቹ፥ ጽኑዓን የነበሩት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች፥ ለእግዚአብሔር ሥራ ሁሉ ለንጉሡም አገልግሎት በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል ባለው በእስራኤል ላይ ተሹመው ነበር። |
እነሆም፥ ለጌታ በሚሆነው ነገር ሁሉ የካህናቱ አለቃ አማርያ፥ በንጉሡም ነገር ሁሉ የይሁዳ ቤት አለቃ የይስማኤል ልጅ ዝባድያ በላያችሁ ተሹመዋል፤ ሌዋውያኑም ደግሞ በፊታችሁ አለቆች ይሆናሉ፤ በርትታችሁም አድርጉ፥ ጌታም መልካም ከሚያደርግ ጋር ይሁን።”
በቀዓት ውስጥም የእንበረማውያን ወገን፥ የይስዓራውያንም ወገን፥ የኬብሮናውያንም ወገን፥ የዑዝኤላውያንም ወገን ይካተቱ ነበር፤ የቀዓታውያን ወገኖች እነዚህ ናቸው።