1 ዜና መዋዕል 26:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከይስዓራውያን ከናንያና ልጆቹ ሹማምትና ፈራጆች እንዲሆኑ በውጭው በሚከናወነው ሥራ በእስራኤል ላይ ተሾመው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከይስዓራውያን፤ ከናንያና ወንዶች ልጆቹ ከቤተ መቅደሱ ውጭ ባለው ሥራ በእስራኤል ላይ ሹማምትና ዳኞች ሆነው ተመደቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከይጽሃር ልጆች መካከል፥ ከናንያና ልጆቹ ከቤተ መቅደሱ ውጪ በመንግሥት ሥራ ሹማምንትና ዳኞች ሆነው ተሹመው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከይሰዓራውያን ከናንያና ልጆቹ ጻፎችና ፈራጆች ይሆኑ ዘንድ በውጭው ሥራ በእስራኤል ላይ ተሾመው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከይስዓራውያን ከናንያና ልጆቹ ሹማምትና ፈራጆች ይሆኑ ዘንድ በውጭው ሥራ በእስራኤል ላይ ተሹመው ነበር። |
ባለ ራእዩም ሳሙኤል፥ የቂስም ልጅ ሳኦል፥ የኔርም ልጅ አበኔር፥ የጽሩያም ልጅ ኢዮአብ የቀደሱት ንዋየ ቅድሳት ሁሉ ከሰሎሚትና ከወንድሞቹ ሥልጣን በታች ነበረ።
በቀዓት ውስጥም የእንበረማውያን ወገን፥ የይስዓራውያንም ወገን፥ የኬብሮናውያንም ወገን፥ የዑዝኤላውያንም ወገን ይካተቱ ነበር፤ የቀዓታውያን ወገኖች እነዚህ ናቸው።
“በአንድ የነፍስ ግድያ ዓይነትና በሌላ፥ በአንድ ዓይነት ሕጋዊ ክርክርና በሌላ፥ ወይም በአንድ የክስ ዓይነትና በሌላ መካከል ውሳኔ የሚጠይቅ ማንኛውም ጉዳይ ቢነሣ፥ ከአቅምህ በላይ የሆነ ጉዳይ በከተሞችህ ውስጥ ቢያጋጥምህ፥ ተነሥተህ አምላክህ ጌታ ወደ መረጠው ስፍራ ውጣ፤