1 ዜና መዋዕል 24:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዳዘዘ፥ አባታቸው አሮን እንደሰጣቸው ሥርዓት ወደ ጌታ ቤት የሚገቡበት የአገልግሎታቸው ሥርዓት ይህ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘውና ከቀድሞ አባታቸው ከአሮን በተሰጣቸው መመሪያ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በሚገቡበት ጊዜ፣ የተወሰነላቸው ሥርዐት ይህ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህም ሰዎች የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የቀድሞ አባታቸውን አሮንን ባዘዘው መሠረት ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው የሥራ ድርሻቸው ክፍፍል ይህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ በአባታቸው በአሮን እጅ እንደ ተሰጣቸው ሥርዐት ወደ እግዚአብሔር ቤት ይገቡ ዘንድ እንደ እየአገልግሎታቸው ቍጥራቸው ይህ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ አባታቸው አሮን እንደሰጣቸው ሥርዐት ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገቡበት የአገልግሎታቸው ሥርዐት ይህ ነበረ። |
ሌዋውያንና ይሁዳም ሁሉ ካህኑ ዮዳሄ ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፤ ካህኑም ዮዳሄ ሰሞነኞቹን አላሰናበተም ነበርና እያንዳንዱ በሰንበት ቀን ይገቡ የነበሩትን በሰንበትም ቀን ይወጡ የነበሩትን ሰዎች ወሰደ።
እንግዲህ በሌዊ ክህነት ፍጹምነት የተገኘ ከሆነ፥ ሕዝቡ በዚያ ላይ የተመሠረተን ሕግ ተቀብለዋልና፤ ወደ ፊት እንደ አሮን ሹመት የሚቆጠር ሳይሆን፥ እንደ መልከጼዴቅ ሹመት የሆነ ሌላ ካህን ሊነሣ ስለምን ያስፈልጋል?