1 ዜና መዋዕል 23:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታን ቤት አገልግሎት በሠሩ ዕድሜአቸው ሀያ ዓመትና ከዚያም ላይ በነበሩ በእያንዳንዳቸው በስማቸው በተቆጠሩት ላይ የአባቶች ቤት አለቆች የሆኑት በየአባቶቻቸው ቤት የሌዊ ልጆች እነዚህ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ እነዚህ የቤተ ሰቡ አለቆች ሆነው እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተመዝግበው የተቈጠሩት የሌዊ ዘሮች ናቸው፤ ዕድሜያቸውም ሃያና ከዚያ በላይ የሆናቸው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚያገለግሉ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ እነዚህ ሁሉ በየጐሣቸውና በየቤተሰባቸው የተዘረዘሩት የሌዊ ዘሮች ሲሆኑ፥ እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተጠቅሰዋል። ኻያ ዓመት የሞላው ወይም ከዚያ በላይ የሆነው እያንዳንዱ የሌዊ ዘር በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ባለው ሥራ ድርሻ ነበረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርን ቤት አገልግሎት በሠሩ ከሃያ አምስት ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ በነበሩ በእያንዳንዳቸው በስማቸው በተቈጠሩት ላይ የአባቶች ቤት አለቆች የሆኑት በየአባቶቻቸው ቤት የሌዊ ልጆች እነዚህ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርን ቤት አገልግሎት በሠሩ ከሃያ ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ በነበሩ በእያንዳንዳቸው በስማቸው በተቈጠሩት ላይ የአባቶች ቤት አለቆች የሆኑት በየአባቶቻቸው ቤት የሌዊ ልጆች እነዚህ ነበሩ። |
ሌዋውያንም ዕድሜአቸው ሠላሳ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ተቈጠሩ፤ በእያንዳንዳንዱ ነፍስ ወከፍ ተቈጠሩ፤ ድምራቸውም ሠላሳ ስምንት ሺህ ነበር።
በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛውም ወር የሸአልቲኤል ልጅ ዘሩባቤል፥ የዮፃዳቅም ልጅ ኢያሱ፥ የቀሩትም ወንድሞቻቸው ካህናትና ሌዋውያን፥ ወደ ኢየሩሳሌምም የተመለሱት ምርኮኞች ሁሉ፥ ሌዋውያንንም ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ የጌታን ቤት ሥራ እንዲቆጣጠሩ መረጧቸው።
በሁለተኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ማኅበሩን ሁሉ ሰብሰቡአቸው፤ እነርሱም ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን አንድ በአንድ እንደየስማቸው ቍጥር፥ በየወገኖቻቸው በየአባቶቻቸውም ቤቶች ትውልዳቸውን መዘገቡ።
“የስምዖን ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች እንደየስማቸው ቍጥር፥ አንድ በአንድ የተቈጠሩት፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን ወንድ ሁሉ፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥
ከእስራኤል ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች የተቈጠሩ እነዚህ ናቸው፤ ከየሰፈሩ በየሠራዊቶቻቸው የተቈጠሩ ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ ኀምሳ ነበሩ።
በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራን ለመሥራት ወደ አገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ዕድሜአቸው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉትን ቁጠራቸው።
ዕድሜው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያለውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራን ለመሥራት ወደ አገልግሎት የሚገባውን ሁሉ ትቈጥራለህ።
“በሌዋውያን ላይ ይህ ተፈጻሚ ይሆንባቸዋል፤ ዕድሚያቸው ሀያ አምስት ዓመት የሆናቸውና ከዚያም በላይ ያሉት የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ለመፈጸም ይገባሉ።